Thursday, August 31, 2017

ሎሬት ቴዎድሮስ ካሳሁን

የትኛውም በህጋዊነት የተቋቋመ ኪነ ጥበባዊም ሆነ ሁለገብ የአለም ላይ ተቋም በራሱ ዘርፍ እጩዎችን አዘጋጅቶ የመሾም ሙሉ መብት አለው። ያን ለማድረግ መስፈርቶች አሉት እነዛን መስፈርቶች ላሟላ ሰው ተገቢውን ክብር እዳይሰጥ የሚያግደው የለም። ለምሳሌ ዩኒሴፍ የአለም የሰላም አምባሳደር እና የአመቱ ምርጥ አባት በማለት ሲሾም እና የአለም ምርጥ አባት ብሎ ሲያከብር አይተናል ቴዲንም የአመቱ ምርጥ አባት ሲል አክብሮታል።
ትላንት ምሽት ነሀሴ 23/12/09/ አቢሲንያ የሽልማት ተቋም በሀርመኒ ሆቴል ባዘጋጀዉ የሽልማትና እዉቅና የመስጠት ስነ ስርአት ለሀገራቸዉ ከፍተኛ ስራን የሰሩ ግለሰቦችን በክብር ሸልሟል። ከነዚህም ዉስጥ የሙዚቃ ጥበባት የሙዚቀኝነት ሁለንተናዊ ክዋኔ የከፍተኛ ክብር ተሸላሚ (ሎሬት) የተሠኘው ሽልማት /ማዕረጋዊ የመጠሪያ ስም/ ለቴዲ አፍሮ ተበርክቷል!! ሎሬት ቴዎድሮስ ካሳሁን ተብሎ ተሰይሟል!
@አምለሰት ሙጬ
Image may contain: 2 people, people smiling

No comments:

Post a Comment