Wednesday, August 30, 2017

የመከላከያና ፖሊስ አመራሮች ውዝግብ በመከላከያ ሃላፊዎች አሸናፊነት ተጠናቀቀ (ነሃሴ 24 ቀን 2009 ዓም)


ትናንት ማክሰኞ ምሽት አንድ የመከላከያ አባል የሆነ መቶ አለቃ በከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተይዞ በባህር ዳር ከተማ የጣና ክ/ከተማ በሚገኘው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰረ ቢሆንም፣ ከመከላከያ ካምፕ የመጡ 3 ባለስልጣናት መኮንኑ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀው ነበር። የወንጀል መከላከል ኢንስፔክተር ሙቀት እና የወንጀል መርማሪ ኢንስፔክተር ቢያምር የተባሉት ፖሊሶች ያሰሩትን መኮንን እንዲፈቱ ሲጠየቁ፣ “መኮንኑ ወንጀል በመፈጸሙ መታሰሩን” በመግለጽ እንደማይፈቱት ከመከላከያ ለመጡት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ከመከላከያ የመጡት ባለስልጣናቱ “አባላችን ልታስሩት አትችሉም” በማለት ሀይል በተቀላቀለበት ሁኔታ ፖሊሶችን ከተናገሩዋቸው በሁዋላ፣ እስረኛው ከታሰረበት ክፍል እንዲወጣ አዘውታል። እስረኛው ጫማውን አድርጎ ሊወጣ ሲል የጣቢያው ፖሊሶች “በወንጀል ያሰርነውን ሰው እናንተ ምን ስለሆናችሁ ነው የምታስወጡት፣ ስነ-ስርዓት ያዙ ካለበለዚያ እንተኩሳለን” በማለታቸው ፣ የመከላከያ ሃላፊዎች ጉዳዩን ለበላይ ለማቅረብ ተገደዋል። የመከላከያ ሃላፊዎቹ ወደ ፖሊስ ኮሚሽን ቢሄዱም “ ህግ እስከፈለገው ድረስ ልንፈታው አንችልም” የሚል መልስ በማግኘታቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰው በፖሊሶች ላይ ዝተው ወደ ካምፓቸው  ተመልሰዋል። Bilderesultat for ወታደሮች

የመከላከያ ባለስልጣናቱ ዛሬ የክልሉን የደህንነት ሃላፊ ፍሰሃ ወ/ሰንበትን ገብተው ያነጋገሩት ሲሆን፣ ፍሰሃም የዞኑን የፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ዳኛውን እንዲፈታው አዞታል። 
በመኮድ የተመደቡ ወታደሮች ገንዘብ አለው የሚባለውን ነጋዴ “ እንድናስርህ ታዘናል፣ የዚህ ድርጅት የፖለቲካ አባል መሆንህ ተደርሶበታል” እያሉ የመገናኛ ሬዲዮና የጦር መሳሪያ በመያዝ እንዲሁም በትግርኛ ቋንቋ በማውራት ከአስፈራሩ በሁዋላ እየተደራደሩ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚቀበሉ የፖሊስ ምንጮች ይናገራሉ። በዚህ መንገድ የተያዙ ወታደሮች በርካታ ቢሆኑም፣ ከመከላከያ ባለስልጣናት ሽፋን የሚያገኙ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ በወንጀል አይጠየቁም።

No comments:

Post a Comment