(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
*****************************በዶ/ር መራራ ጉዲና እና በሌሎችም የህሊና እስረኞች ላይ የሚታየውን የከፋ አያያዝ በመቃወም እንዲሁም ከግብርና ከአስተዳደር ብልሹነት ጋር በተያያዘ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬም የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ ነው። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅትም ሆነ አዋጁ ከተነሳ በኈላ አድማ ሲያደርግ የከረመው የአምቦ ከተማ ህዝብ፣ ዛሬ ደግሞ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ የታሰሩ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቋል። በወሊሶም ተመሳሳይ አድማ ሲካሄድ
በሰሜን ወሎ ወልድያ ፣ መርሳ፣ ላሊበላና ሌሎችም ከተሞች፣ በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ፣ በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከተማ የስራ ማቆም አድማዎች ሲካሄዱ ውለዋል። አድማዎቹ በዘፈቀደ ከሚጣለው ግብር ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ተቃውሟቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው።
በነጋዴዎች ድርጊት የተበሳጨው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የንግድ ድርጅቶችን ማሸግ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል። እርምጃው ከብስጭትና ተስፋ መቁረጥ የመጣ ነው የሚሉት ድርጅቶቻቸው የታሸጉባቸው ነጋዴዎች፣ ድርጊቱ በትግላቸው እንዲገፉበት ለበለጠ ትግል የሚያነሳሳ እንጅ የሚያሸማቅቅ አይሆንም ይላሉ።
በዶ/ር መራራ ጉዲና እና በሌሎችም የህሊና እስረኞች ላይ የሚታየውን የከፋ አያያዝ በመቃወም እንዲሁም ከግብርና ከአስተዳደር ብልሹነት ጋር በተያያዘ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬም የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ ነው። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅትም ሆነ አዋጁ ከተነሳ በኈላ አድማ ሲያደርግ የከረመው የአምቦ ከተማ ህዝብ፣ ዛሬ ደግሞ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ የታሰሩ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቋል። በወሊሶም ተመሳሳይ አድማ ሲካሄድ
በሰሜን ወሎ ወልድያ ፣ መርሳ፣ ላሊበላና ሌሎችም ከተሞች፣ በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ፣ በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከተማ የስራ ማቆም አድማዎች ሲካሄዱ ውለዋል። አድማዎቹ በዘፈቀደ ከሚጣለው ግብር ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ተቃውሟቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው።
በነጋዴዎች ድርጊት የተበሳጨው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የንግድ ድርጅቶችን ማሸግ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል። እርምጃው ከብስጭትና ተስፋ መቁረጥ የመጣ ነው የሚሉት ድርጅቶቻቸው የታሸጉባቸው ነጋዴዎች፣ ድርጊቱ በትግላቸው እንዲገፉበት ለበለጠ ትግል የሚያነሳሳ እንጅ የሚያሸማቅቅ አይሆንም ይላሉ።
No comments:
Post a Comment