Monday, August 28, 2017

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ላይ ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውጊያ መደረጉ ተገለጸ (ኢሳት ዜና–ነሐሴ 22/2009)

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ላይ ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውጊያ መደረጉ ተገለጸ።
በሶማሌ ልዩ ሃይልና በኦሮሞ አርሶአደሮች መካከል በተደረገው ውጊያ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው የታወቀ ሲሆን አንደኛው የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ወደ አዳማ ሆስፒታል መወሰዱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ውጊያው መኢሶን በተባለች ከተማ አቅራቢያ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች መካሄዱ ተገለጿል።

በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የተሳካ የአድማ ጥሪ ያደረጉት የኦሮሞ ወጣቶች በቀጣይ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወጣቶች ጋር ለመስራት እየተዘጋጁ መሆናቸውን በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል።
ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ በአንዳንድ አከባቢዎች ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ግጭት የተፈጠረ ሲሆን መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
@ምስል ከፋይል

No comments:

Post a Comment