Friday, August 11, 2017

በአርበኞች ግንቦት7 እና በስርዓቱ ወታደሮች መካከል ውጊያ ተካሄደ


ኢሳት ዜና ( ነሃሴ 05 ቀን 2006 ዓም) 
ነሃሴ 5 ቀን 2009 ዓም ጠዋት ላይ በበለሳ ቆላ ሃሙሲት፣ ጣይመን በሚባል ቦታ ላይ በአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮችና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። በተኩስ ልውውጡ ከአገዛዙ ወታደሮች አንድ ሰው ሲገደል፣ ከአርበኞች በኩልም አንድ ሰው መሞቱን ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
አርበኞች ግንቦት7 ዘግይቶ ባወጣው መግለጫ ደግሞ 3 የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ገልጿል። አንደኛው አስከሬን ሃሙሲት ከተማ ላይ መቀበሩን ገልጿል። 
በገዢው ፓርቲ በኩል ስለደረሰበት ወይም ስላደረሰው ጉዳት የገለጸው ነገር የለም።

No comments:

Post a Comment