Thursday, August 10, 2017

በባቢሌና ሃረር መካከል ከፍተኛ ግጭት መነሳቱን አሜሪካ ኢምባሲ አስታወቀ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


ኢምባሲው ባወጣው መግለጫ ከአዲስ አበባ ወደ ጅጅጋ የሚወስደው መንገድ ባቢሌና ሃረር መካከል ላይ ተዘግቷል። በጦር መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ ግጭት እየተካሄ መሆኑን ኢምባሲው ገልጿል። የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው አምርተዋል። መንገዶች በመዘጋታቸው ወደ አካባቢው መንቀሳቀስ አይቻልም። የአሜሪካ ዜጎች ወደ ባቢሌና ሃረር እንዳይጓዙ ኢምባሲው አስጠንቅቋል። 
የአሜሪካ ኢምባሲ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ኢሳት ባደረገው ማጣራት ከሃረር 55 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ቆሬ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግጭት ሲካሄድ መዋሉን አረጋግጧል። ግጭቱ ከሶማሊና ኦሮምያ ክልሎች ድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ መነሳቱ ታውቋል። አሁንም ድረስ አካባቢው ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን አካባቢው ሰዎች ለመረዳት ተችሏል።

No comments:

Post a Comment