Saturday, September 5, 2015

በመቀለ ከተማ

በመቀለ ከተማ 
ሲካሄድ የቆየው የህወሃት ጉባኤ ኢ-ዲሞክራሲያዊና የይስሙላ እንደነበረ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ከጉባኤው ተሳታፊዎች ካገኙት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።በጉባኤው ከተሳተፉ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ከማዕከላዊ ኮሚቴነት በራሳቸው ፈቃድ ተሰናበቱ የተባሉት ነባር ታጋዮች ለሚዲያ ሽፋን ሲባል ድርጂቱን ዲሞክራሲያዊ ለማስመሰል እንጂ ከሁለት አመት በፊት በማዕከላዊ ኮሚቴዎች መካከል የተፈጠረ ልዩነትና አለመግባባት ምስቲሩን ለማጥፋትና ለመደበቅ የተጠቀሙበት የቡድኑ የይስሙላ አካሄድ መሆኑን ታውቋል።

መረጃው ጨምሮም ከነሃሴ 12 2007 ዓ/ም ጀምሮ የተካሄደ ጉባኤ ኢ-ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ይከተል ስለነበር በጉባኤው የህወሃትን ድርጂት የሚመራው ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል መሆን አለበት የሚል በ20 የእጅ ብጫ አሸንፎ እያለ መቀነስ አለባቸው ከተባሉት መካከል አቶ አባይ ወልዱ አንዱ መሆኑ እየታወቀ በኢ ዲሞክራሲያዊ አካሄድ ህወሃት ማሌሊትን በሊቀመንበርነት እንዲመራ በይስሙላ ያሸነፈ አስመስለው እንዳቀረቡትና በጉኤተኛው መካከልም የተፈጠረውን አለመግባባት ለማብረድ ጊዜ ተሰጥቶት ሊጠናቀቅ መቻሉን ለምወቅ ተችሏል።mekelle gubae tplf 12

No comments:

Post a Comment