Sunday, September 6, 2015

ለአርበኝነት ደጀንነት በሲዊዘርላንድ – የመንፈስ ኪዳን በድንቅነት የሀገር ማዳን ውል ታሰረበት። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46438#sthash.ElBrFSoh.dpuf

finland
የምልዕቱን ከሥርጉተ ሥላሴ 05.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/ „ግንቦት 7 ቀን  1997 ዓ.ም ላይ ሆኖ ኢትዮጵያን ያዬ ሰው ግንቦት 7 ቀን 1998ዓ.ም ሲመለከታት ተስፋው በጨለማ ሊዋጥበት ይችላል። ግን አተኩሮ ለተመለከተው የአጭር ጊዜዉ የጨለመ ይምሰል እንጂ የረጅሙ ጊዜ የኢትዮጵያ ተስፋ ብሩህ ነው። የአርበኛ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ቃል (የነፃነት ጎህ ሲቀድ መጸሐፍ ገጽ  614)“ ዛሬ መስከረም 5. 2015 በሲዊዘርላንድ ውብ ከተማ በዙሪክ ገማይንሻፍትስሴንትረን ኢትዮጵያዊነትን መሪው ያደረገ፤ ብሄራዊ ኃላፊነትን በጥሞና የተጋራ፤ ህዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46438#sthash.ElBrFSoh.dpufቀልብ የሳበው የአርበኞች ግንቦት 7 የተግባር ውሎ ለብሄራዊ የነፃነት ራህብተኛው ልዩ ስጦታ በመሆኑ፤ የተሳትፎው ዓውድ ሙሉዑ ነበር ማለት ይቻላል። ይህ ብሄራዊ ስብሰባ የድንቅነቱ ድባብ ፍጹም ሳቢ ካደረጉት ታላቅ አምክንዮ ውስጥ፤ የቅዱሱ ሰማእት የአባታችን የአቡነ ዼጥሮስ የአደራ ዓይን የሆኑት ቅዱሱ አባታችን ብጹእ አቡነ መቃርዮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ የኩቢክ ካናዳ የአውስትራልያ፤ የቅድስት ሀገር የእስራኤል እዬሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ፤ እንዲሁም የአውሮፓና የአፍሪካ ምክትል ሊቀ ጳጳስ በመሃከላችን ተገኝተው ጉባኤውን በቃለ ምህዳን ባርከው መክፈታቸው ብቻ ሳይሆን፤ በሀገረ ሲዊዝ የአርበኝነት አብነታዊ የትምህርት ተቋም መክፈታቸው፤ ስብሰባውን ለመታደም፤ ልዕልታቸውን ኢትዮዽያን ሃይማኖታቸው ላደረጉ ቅን ኢትዮጵያውያን ወገኖች ሁሉ የምርቃት ቀለበት ማዕልት ነበር ማለት እችላለሁ። ብሩክ የተባረከ። በዚህ መራራ ዘመን ይበቃኛልን ታጥቆ እኔም ከልጆቼ ጋር ልዘምት ዝግጁ ነኝ ያለ ቃለ ህይወት እንሆ በታሪክ እንዳነበብነው ዓይናችን – በዓዬናችን አየን።  በቀደምቷ ሀገር በናፍቆት ኢትዮዽያ ሚስጢር እንዲህ እንደ ኤዶም ወንዞች መንፈስን ያድሳል። „እሄዳለሁ …  እሄዳለሁ …. እሄዳለሁ …  እሄዳለሁ  – ወደ አርበኛ ልጆቼ።  ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚህ መልክ አንገናኝም„ ሲሉ አባታችን ዕንባ – ሲቃና እልልታ ዓውደ ምህረቱን የቅኔ – ዘጉባኤ እልፍኝ አደረጉት“  በዚህ ሁለመናው ጠፍ በሆነው በወያኔ ኃርነት ትግራይ ፋሽስታዊ  ዘመን – ለአንድ የወንጌል ገበሬ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ፊደል ሆና ሳዬ የመጀመሪዪ ስለሆነ ፀሐይ  የወጣችበት ቀን ነው – ልበል። አርበኞቻችን ቀን ሰጥቷቸዋል። የድል ዋዜማ – ለእማማ። የስብሰባው መንፈስ እራሱ ንዑድ፤ ከአለም ትርኪ – ምርኪ – የወጣ፤ በተደሞ – የተዋበ፤ የልቤ ቀለበት ነበር። እውነት ለመናገር የፈላስማው የአርበኛ አንዳርጋቸው መንፈስ የማያንቀላፋ ቆቅ መሆኑን – ከገሃዱ ዐለም በበለጠ መንፈሳዊ ሃዲዱ በሥነ – ጥበቡ በውስጥነት መንፈስ ደምቆ ታነጸ። ተመስገን። በተጨማሪም ይህ ርቁቅ ሰማያዊ ትንግርት እትብቱን – አይተን፤ ትንፋሹን  – አዳምጠን፤ ስስታችን ሆነ  ናፍቆታችን በመስተጋብር መንፈሱን – ከመንፈሳችን፤ የጎለጎታ ስቃዩን በምልሰት እንቃኝበት ዘንድ ቤተ – አርበኛ አካሉ የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ ሀገር ከፍተኛ አመራር አካል የሆኑት የተከበሩ አቶ ብዙነህ ጽጌ በመካከላችን  – ተገኙ። ሁለት የእግዚአብሄር መልእክተኞች ለእኛ  – ተላከልን። ወደ አርበኞቻችን ሙቅ „የበቃን ህወሓት“ ሙሉ ስሜታችነን አደራ ተቀብሎ መልእክት አዱራሽ ሐዋርያ በአንድ በኩል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የመንገድ ጠራጊው የጀግና አንዳርጋቸው ጽጌ ረቂቅ የመንፈስ አካል የሥጋ ወንድም የትግል አርማ ሁነኛ መንፈስን – በመንፈስ አድራሽ ቤተኛ መቸቱ በመሆን ሁነኛ ታተመ። ዕጹብ ድንቅ። አዲስ ዐመት ዘንድሮ ብቻ ለእኔ አዲስ ከወትሮው የተለየ ነው። የኢትዮጵያዊነት ፍጽምና ፉፍቶ፤ ለምልሞ የታደሰበት በተግባሩ የነጠረ ሁለገብ ሥህነ – ሙሤ የተሰጠንበት፤ የእናት ሀገራችን የኢትዮጵያ ዕንባ ቤት ያገኘበት – የተናኘበት፤ አርበኛው ብቁ የአስተዳደር መሪወቹን ብቻ ሳይሆን ታቦቱን የተሸለመበት ነገ የነጋበት – የበራለት ዘመን ነው፤ በተጨማሪም ሙቅ የህወሓት „በቃን“  ከወትሮው የተለየ ነበር። በዚህ ለብሄራዊ ነፃነት የራስ እርቅ ባፋጠጠበት ደመ ግቡና ደመ ሞቃት ቀን ብጽዕ አባታችን ትውፊተ – ጀግንነትን ሲቀልቡን፤  የተከበሩ አቶ ብዙነህ ጽጌ ደግሞ የተስፋችን መዳረሻ በሁለገብ መክሊት፤ የመንገዳችን ትልም ምን መምሰል እንዳለበት፤ የግልና የወል ድርሻችነን በአጽህኖት አብራርተዋል፤  ታዳሚዎችም ውስጥን ውስጥ ያደረገ በእኛነት መንፈስ የተሳትፎውን አድማስ ሰፋ  – አድርገውታል።  የሥነ – ጥበብ ቤተሰቦች ደግሞ ብራናውን በህሊናዊ አድዮ ምርት – አንቆጥቁጠውታል። እንቁጢ እኮ ደረስኩባችሁ እያለች ነው። በጭምቷ ሲዊዝ የሚኖሩ የሴት አረቂዎቼ – የተግባር እመቤት እህቶቼ ማለፊያ መስተንግዷቸው መሸቢያ ነበር፤ የዶሮ ዳቦም አልቀራቸውም። የአውዳመቱ ዋዜማ በስንዱ እህቶቻችን እምር – ስምር አለ። በአርበኝነቱ የደጀንነት የእጅ ካቴና – ሀብሉ ሽልንጉንም ገፋ አድርገው እኩልነታቸውን በተባ ተግባር  – አስጌጡት። ድንቆች። በቅዱስ አባታችን መሪነት በነፍስ ወከፍ የእርዳታ አሰባሰብ በሚገርም ሁኔታ በ2500.00 CH ነበር የተጀመረው ከዛማ ምን እነግራችሁአለሁ 1500.00 CH 1000.00 CH 500.00 CH በጣም ብዙ ጀግኖች ነበር ለዚህ ጫን ላለ ልግስና እና በረከት የተሰለፋት። ሀገርን የማዳኑ ጥሪ ባለቤትነቱ ህዝባዊ መሠረቱ – በተግባር ትርጉም ተመሳጠረ። ባለመቻል ያልመጣችሁ የመንፈስ ስንቅና ትጥቅ – ቀረባችሁ። ቅኑ። አሃ! በጨረታውም ጥቂት የማይባሉ ባውንዶች በወረፋ ተስልፈው ሲፎካከሩ ከቆዩ በኋላ፤ አሸናፊው የጀግናውን መንፈስ ድሉ የእኛ ነው አለ፤ በዚህ ስብሰባ ያዬሁት መልካም ነገር ፊት ለፊት ወጥተው የሚያታግሉት ወገኖቼ የተሰባሰበ ፍላጎት ላይ በአኃቲ መንፈስ ከትመው አይቻቸዋለሁ። ይህ ልዩ – ሥልጡን – የአቅም ግንባታ መንገድ ነው፤ ማለፊያ።  በመጨረሻም በቀሲስ አበባው አዳነ የነፃነት ትግልና ቃለ- ወንጌልን ያስማማ ጠቃሚ አስተያዬት  – ተሰጥቷል። የብሄራዊ የነፃነት ትግላችን የሥነ ልቦና መንፈስ – ገዢ መሬት ላይ ያረገበት ደቂቃ እጅግ ያስቀና ነበር፤ እነ ሦስቱ የአርበኛ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ  አርበኛ ነአምን ዘለቀ አርበኛ ኤፍሬም ማዲቦ ያሉበትን በአርብኝነት ዜማ ቅኝቱን ቴክኖሎጂው ሲያመጣው ሲቃው – የፍቅር ምት ትርታው  – እንባው – አዲስ ህይወት ነበር፤ በህይወት መኖር አጀንዳዬ ሆኖ ለማያውቀዉ ለእኔ እራሱ – ለመኖር ሳሳሁለት፤ እንኳንስ – ለሌላው፤ ዛሬ ረቂቅ ነበር፤ ይሄ የስብሰባ ፕሮቶኮል – የስብሰባ ፕሮሲጀር – የባለቤትነት ምንትስ አልነበረም፤ ሐሤት ግን ተመስጥሮ ነበር፤ እመቤት ኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን –  ሰው አላት። ትኖራለችም – ለዘለዓለም። ተመስገን። ክወና  – ጉባኤው በሁለገብ መሰናዶ – ቤተሰባዊ ተሳትፎውን አጉልቶና አጎልብቶ – የድርሻውን በማሟላት – ተልዕኮውን በጀግና አንዳርጋቸው ጽጌ የመንፈስ ጥሪት፤ ለእኔ ብሄራዊ መዝሙሬ በሆነው „ለአንች ነው ኢትዮጵያ“ ጽዑመ ዜማዊ መዝሙር፤ በላቀ የአርበኝነት ስሜትና ወኔ፤ እንዲሁም በብሄራዊ የነፃነት ትግሉ የሥነ – ልቦና የበላይነት ተጠናቋል። ባንዳ ሰላይ – አስመሳይም – ይፈር፤ የህወሓትን ፍርፋሪ እየለቃቀመ ታቱ ዥግራ – ይበል። ሴራው የድቡሽት ቤት ሆኗል። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46438#sthash.ElBrFSoh.dpuf

No comments:

Post a Comment