Sunday, September 6, 2015

አል_ሸባብ የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አጠናክሮ ቀጥሏል



አል_ሸባብ የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አጠናክሮ ቀጥሏል
በ 04/09/2015 አርብ አልሸባብ የፍሪካ ህብረቱን ሰራዊት አጥቅቶ ሁለት ቁልፍ ከተሞችን ተቆጣጠረ። ስማሌን እያስተዳደረ የሚገኘዉ መንግስት ቃል አቀባይ አሊ ኑር ለሮይተር እንዳሳወቀዉ በደቡብ ምእራብ ሶማሌያ ኢል_ሳሊኒዲ (EL-SALIINDI) እና ኩንትዋሬ (KUNTUWAREY) የተባሉ ከተሞችን አል ሸባብ ከህብረቱ ሐይል ነጥቋል::
በጦርነቱ የኢትዮፕያ ወታደሮች በብዛት ለሞትና ለከፍተኛ መቁሰል አደጋ መዳረጋቸዉን ጨምሮ ምርኮም መሆናቸዉ ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ለደቡብ ሞቃዲሾ 65 ኪ/ሜ የሚቀረዉን እና ለማራክ ወደብ ( MARAK PORT ) ማለፊያና ቅርብ የሆነዉን ኢል_ሳሊንዲን ከተማ እንዲሁም ለባራዌ ወደብ (BARAWE PORT) መተላለፊያና ቁልፍ የሆነዉን ኩንትዋሬን ከተማ በጁ ያስገባዉ አል_ሸባብ አለምንና የሰረ ሽብር ትብብር ሐገራትን አስደንግጧል።
20 ሺ የሚጠጋ የአፍሪካ ህብረቱ ሰራዊት ሊያጸዱት ያልቻሉት አል_ሸባብ በተለያየ ወቅቶችና ሰአቶች ድንገኛና አደገኛ ጥቃት እንደሚፈጽም የሚታወቅ ሲሆን በተልይም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ጥቃት ኢላማ ዉስጥ በማስገባት ተደጋጋሚ ጥቃት አድርሷል በቅርቡ የኡጋንዳ መንግስት በአል_ሸባብ የተግደሉበትን ወታደሮች በክብር የቀበረ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በየቀኑ እየተገደሉና የሶማሌ በረሐ እራት እየሆኑ ባሉበት በዚህ አደገኛ የጦርነት ወቅት ለዜጎቹና ለመከላከያ ሰራዊቱ ደንታ የሌለዉ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ጨካኝ ቡድን አንድም ነገር ተንፍሶ አያዉቅም።
ከአርብ እለት ጀምሮ በተደረጉ የሶማሌያ አልሸባብ _ አሚሶ ጦርነቶች ቁጥራቸዉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ተሰዉተዋል።
ጉድሽ ወያኔ..

No comments:

Post a Comment