Thursday, October 1, 2015

የወያኔ ጄኔራሎች እና የደህንነት ሃላፊዎች በመጭው ወር ስብሰባ ሊቀመጡ ነው::
ስብሰባ የማይሰለቸው የበሰበሰው የወያኔ አገዛዝ በስርኣቱ ላይ የተጋረጡትን አደጋዎች በተመለከተ ለመወያየት ከየክልሉ እና ከየጦር ክፍሉ የተሰበሰቡ ባለከፍተኛ ማእረግ ወታደራዊ አዛዦች እና የደህንነት ባለስልጣናት በመጭው ወር ስብሰባ እንደሚቀመጡ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::ይህ ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ ታስቦ የነበረው ስብሰባ በተደራራቢ ስራዎች ውጥረት እንዲረዝም መደረጉ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::
በአገዛዙ ላይ ተደቅነዋል የተባሉ ከባድ ሃላፊነት እና መስዋትነት የሚጠይቁ ችግሮች ዙሪያ ለመወያየት በመጪው ወር የተጠራው ስብሰባ በዝግ እንደሚካሄድ እና መቅረጽም ይሁም ማስታወሻ መያዝ እንደሚከለከል ቅድሚያ ማስጠነቀቂያ የተሰጠ ሲሆን በአገዛዙ ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እና ችግር እጅግ አጣዳፊ መፍትሄ ከመሻቱም በላይ ወታደራዊ እና የደህነት ተቋማትን በምስጢራዊ ስልት የማደራጀት እቅድ ይነደፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ የገለጹ ሲሆን በወያኔ ላይ የተደቀነው አደጋ ሕዝቡ እና ለጋሽ አገሮች ፊታቸውን ከማዞራቸው ጋር ተደምሮ መጭው ጊዜ አስጊ መሆኑን ምንጮቹ ያገኙትን መረጃ ተናግረዋል::

የወያኔው ስርኣት በከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ አገዛዙ የተረጋጋ እና በልማት ጎዳና ላይ ነው ቢሰብክም ያለው እውነት ግን ከሚሰበከው ፕሮፓጋንዳ የተለየ እና የወያኔው አገዛዝ ከፍተኛ የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለ ሲጠቁም የተቃዋሚ ፓርቲዎች/የለውጥ ሃይሎች ይህንን አጋጣሚ ለመጠቀም ሕዝብን ለማደራጀት መንቃት እንዳለባቸው እንዲሁም ከዚህ ቀደም የአገዛዙ መንገዳገድ ሊጠቀሙበት ያልቻሉ ሁሉ ተጠናክረው በስርኣቱ ላይ የሚደረጉ ትግሎችን ለድል እንዲያበቁ ያለው ጊዜ አመቺ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል::

No comments:

Post a Comment