Thursday, October 1, 2015

Girum Teklehaimanot

 እውነትን ፍለጋ....
እግዚአብሔር አሸናፊ ነው ከተቀነባበረብኝ ሴራ አውጥቶኛል
በግሩም ተ/ሀይማኖት
ኤምባሲ በር አጠገብ ጎዳና የወደቁ ወገኖቼን በቻልኩ ጊዜ ምግብ የማበላቸውን በማስተባበር የሀሰት ክስ ከፈቱብኝ። ከሳሾቼ በአጠቃላይ በችግራቸው ጊዜ አይዟችሁ ያልኳቸው ሲሆኑ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ሁለት ሀይሎች ከኋላቸው መሰለፋቸውን ለማረጋገጥ ችያለሁ። 
አንደኛው ሀይል በUNHCR ስር ላሉት ስደተኞች ከዚህ ጦርነት በህይወት የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻችት ከአንጋፋዋና የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሞዴሊስት የሀረር ወርቅ ጋሻው ጋር ባለኝ ግንኙነት ጥሩ ያልተሰማቸው ወገኖች ናቸው። 
ሁለተኛ ጎዳና ላይ ከወደቁት መካከል በሀሰት አታለው እንዲመሰክሩ ካነሳሷቸው መካከል "እኛ አታለውናል ይሄ ሰው ያለውን በአቅሙ አብልቶናል። ለበአል እለት ፎቷችሁን በኢንተርኔት በትኖ ገንዘብ ሰበሰበ ብለው አታለውን ነው። እንዲያውም ትላንት ባልሽ እስር ቤት ሲገባ ማታ ላይ የኤምባሲ ሰራተኛ የሆነው ሀዲሽ የሚባለው እና አንድ ሰው የምንተኛበት ድረስ መጥተው ነበር። 
"...ይህን ሰው እንዳትለቁት ኢትዮጵያም የሚፈለግ ወንጀለኛ ጋዜጠኛ ነው እኛ ከኋላ እናግዛችኋለን..." አሉን። ብዙ ሲናገሩ በጥላቻ ተነሳስተው እንዳሳሰሩት የተወሰነው ገባን። ተነጋገርን ይሄ ሰው ባበላን ለምን እንመሰክርበታለን? ያሉት ገንዘብ እንደተላከም አናውቅም ብለው ለሚስቴ ቃላቸውን ሰጥተዋታል። እንድትቀዳም ፈቅደው በሞባይል ስልኳ ቀድታቸዋለች።...ለፖሊስም ይህንኑ ቃል ሰጥተዋል። 
በሀሰት የወነጀሉበት ማስረጃም ተቀባይነት አጥቷል። እግዚአብሔር የእውነት ሀያል አምላክ ነው። ስለእውነት ድብቁን ገሀድ የሚያወጣ...እኔም ከተቀናበረብኝ የሀሰት ማስረጃ ነጻ አወጣኝ።
ከምንም በላይ የምውደው የማከብረው በርታ ለወገናችን ድምጽ መሆናችን ከህሊና ወቀሳ ያድነናል የሚለኝ ወንድሜ ነብዩን በዚህ ጊዜ ልሳኔ በተሸበበበት ወቅት ድምጽ ሆኖኛል። ነብዩ ምን ጊዜም እኮራብሀለሁ...የሀብታሙ አሰፋ ነገር ዝም ነው ሁሌም አበረታቼ በቅርብ ያለ ወዳጄ ነው። ምስጋናዬ ይደረሰው...ሰርካለም ፋሲል ምርጥ ወደር የሌላት እህቴ የሞያ አጋሬ..ምስጋናዬ ከልብ ነው። መሳይ..ፋሲል የኔ አለም በአጠቃላይ ኢሳቶች አቦ ብዝት ትርፍርፍ ያርጋችሁ..የህዝብ ድምጾች። ዳዊት ከበደ..ዘላለም ገብሬ.. .ስንታችሁን ልዘርዝር ሲከፋኝም እናንተው ላይ የተሰማኝን ዘርግፌ አብራችሁኝ አላችሁ ያቆያችሁ። 
ሁሉንም ማህበራዊ ድረ-ገጾች ሁሉንም የሞያ ጓደኞቼን ኮርቼባችኋለሁ። ይህን ያህል ሰው ከጎኔ መሆኑን ያወኩበት አጋጣሚ በመሆኑ ደስ ብሎኛል መታሰሬ ያደናገጣችሁ ያለቀሳችሁ ሁሉ ሀያሉ እግዚአብሄር ይመስገን በሉ።

No comments:

Post a Comment