ኢትዮጵያ ያላችሁ እና በዓለም ዙርያ የምትገኙ ኢትዮጵያኖች እነዚህን ልማታዊ አርቲስቶች በ 4 ነጥብ ልትዝፕጓቸው ይገባል.
አርቲስት ማለት የህዝብ ነው. አርቲስት ህዝብን በስራው ያዝናናል, ያፅናና ል, ያበረታታል, ያፋቅራል እንጂ ከመንግስት ጋር ወግኖ ያውም ህዝብን ንቆ ምን ታመጣላችሁ ብሎ ከሚረግጥ ጋር አይወግንም. ጡሩንባም አይሆንም.
አንድ ወጣት የተናገረችው ምንም ልረሳው የማልችል ነገር አለ. ይቺ ወጣት እንዲህ አለች የኢትዮጵያ አርቲስቶች በሚድያ ላይ ቀርበው ገቢያችሁ ወይም ሃብታችሁ ሰንት ነው ስትባሉ ሃብታችን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ትላላችሁ. ህዝብ እና ሃገር ሲጣፋ ግን ዝም ትላላችሁ. እውነት የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብታችሁ ከሆነ ምነው እንዲህ ሲባክን እና ሲጠፋ ዝም አላችሁ? ሃብታችሁ ከሆነ ለምን አትሰበስቡትም ነበር ያለችው. ይህ አባባል ትክክል ነው.አርቲስት ጥበበኛ ነው. በጥበቡ ብዙ ማስተማር እና ማሳወቅ ይችላል. ለምሳሌ እኔ በግጥም, ታሪካዊ በሆኑ ፅሁፎች, በድራማ እና በተለያዩ ዘፈኖች ብዙ ነገሮችን ቀስሜያለሁ. ነፍሱን ይማር እና ዶ / ር ጥላሁን ገሰሰ ኢትዮጵያዊነትን እና ወገንተኛዊነትን በደማችን ያሰራጨብን የለም. አዎን የጥንቱ ዶ / ር ጥላሁን የዛሬው ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁንን የሚያክል ማንም የለም.
ኢትዮጵያውያኖች ሆይ !!!! ሆድ አደር ልማታዊ አርቲስቶች ላይ መቼ ይሆን ጀርባችሁን የምታዞሩት? የነሱ መበልፀግ እና እብዲህ ገኖ መታየት በናንተ መሆኑን አታውቁም? ሃብቴ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ብለው ከአምባገነኖች ጋር ሲያሽቃብጡ ማየትስ አልደከማችሁም? መቼ ነው የናንተ ነገር በቃንስ የምትሉዋቸው? ኧረ በቃ !!
(የኢትዮጵያ ሁለት ጡቶች በቂ ወተት መያዝ ጀምረዋል እርሶ በስፍራው ይገኙ እንጂ አወራረዱን በሚገባ እናሳዮታለን …….. ያሉን ሁለት አዋቂዎች)
- See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10569#sthash.XquAB5ol.dpuf
No comments:
Post a Comment