Monday, November 30, 2015

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በፌደራል ፖሊስ ተደብደበው ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ የተወሰኑት ፎቶዎች ተለቀዋል -

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ የተማሪዎች ተቃውሞ የፌደራል ፖሊስ ግቢ ውስጥ ገብቶ በርካታ ተማሪዎችን በሰደፍ እና በዱላ ሲቀጠቅጥ ነበር:: ከፖሊስ ጥይትና ዱላ ለማምለጥ ከ3ኛ ፎቅ የዘለሉ ተማሪዎችም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የሚመጡ መረጃዎች ያስታውቃሉ:: እስከሁን ከ40 የማያንሱ ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአይን እማኞች ሲገልጹ የሞቱት ቁጥር እስካሁን የታወቀው 3 ብቻ ነው::
የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም ተማሪዎቹ ባነሱት ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ መደናገጥ ውስጥ የገባው ሕወሓት የሚመራው መንግስት በፌደራል ፖሊሶች አማካኝነት ጉዳት ማድረሱን ቀጥሎበታል:: የተማሪዎቹ አመጽ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች እየተንሰራፋ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውጥረቱ እንዳየለ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አስታውቀዋል::
በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሆስፒታል – ፎቶዎች ይመልከቱ
Haromaya 2haromaya 3Haromaya 4

ኢሳት ዜና


ተጨማሪ መረጃ ከሃሮማያ
ሁለት ተማሪዎች ከፌደራል ፖሊስ ዱላ ሲሸሹ ከ3ኛ ፎቅ ለመዝለል ሞክረው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለህይወታቸው አስጊ እንደሆነ የሀረር የሆስፒታል ምንጮች ገልጸዋል። ከ30 በላይ ተማሪዎች ታፍሰው ወደ እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን በሃሮማያ ካምፓስ መንገድ ላይ የተገኘ ተማሪ ሁሉ በተመሳሳይ እየታሰረ ነው። ከመኝታ ክፍሉ ማምሻውን ያነጋገርነው ተማሪ ''..ለህይወቴ ሰግቼአለሁ። የኦሮሚያ ፈጥኖ ደራሽና የፌደራል ፖሊስ በር እየሰበሩ እየደበደቡ ናቸው። ሴቶችንም መኝታ ክፍላቸው ገብተው እየደበደቧቸው ነው። በጣም አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው።..'' ብሏል። ወደ ሀረርና ድሬዳዋ የሚያመልጡ ተማሪዎች ኬላ ላይ ተይዘው ወደ እስርቤት መወሰዳቸውም ታውቋል። የሃሮማያውን እንቅስቃሴ እየተከታተልን እንዘግባለን።.

ኢሳት ዜና

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰውን የተማሪዎች አመጽ በተመለከተ መረጃዎች እየደረሱን ነው። ግቢው በፌደራል ፖሊስ ተወሯል። ወደ ዩኒቨርስቲው የሚወስዱት መንገዶች ተዘግተዋል። የፖሊስ ሃይል ተጨማሪ ወደ ግቢው እየተጠጋ ነው። በድሬዳዋ ካምፓስም በተመሳሳይ አመጽ ተቅስቅሷል። በርካታ ተማሪዎች ታስረዋል። በሌሎች ካምፓሶች ውጥረቱ እንደጀመረም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ለጊዜው ቁጥሩ ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም የተገደሉ ተማሪዎች እንዳሉ እየተነገረ ነው። ኢሳት በዚህ ዙሪያ ማጣራት እያደረገ ነው። በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞችም ቀጥሏል። በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ዘገባ ይኖረናል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አውሮፓ ፓርላማ ድርቁን አስመልክቶ ለንግግር መጋበዝ ምዕራባውያን ለሚደረገው የትጥቅ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተባለ ፣

የሱዳን ዲፕሎማት አወዛጋቢው መሬት ቀድሞም የኢትዮጵያ ሳይሆን እኛ የሰጠናችሁ ነው ሲሉ ተናገሩ ፣የአማራ ክልል ባለስልጣናት ታጣቂዎችን እያደራጁ አስወጉን ሲሉ አወገዙ፣ የአባይ ወንዝን በተናጠል መገንባት እና መጠቀም ጦር ሊያማዝዝ ይችላል ተባለ፣በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅና ረሃብ አገሪቱንና ሕዝቧን እየተፈታተነ መሆኑ ተነገረ፣የጋሞ ብሄርን የሚያንቋሽሽ መጽሐፍ መውጣቱን ከተቃወሙ ውስጥ ዋና ዋና አስተባባሪ የተባሉት 69 ሰዎች በግንቦት ሰባት ስም ተወንጅለው መታሰራቸው ተገለጸ፣የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አውሮፓ ፓርላማ ድርቁን አስመልክቶ ለንግግር መጋበዝ ምዕራባውያን ለሚደረገው የትጥቅ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተባለ ፣ በአገር ቤት በበጎ ፈቃደኞች በረሃቡ የተጎዱትን ለማገዝ የተቋቋመው <ቤዛ እንሁን> ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፣በመምህር ግርማ ጉዳይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወልቃይት ቀፍታ፣ አድ ኸርዲ፣ አፀ ሐርማዝ፣ አድ ፀፀርና በሌሎችም ትንንሽ ከተሞች በመዘዋወር ለሁለት ተከታታይ ሌሊቶች በራሪ ፅሁፎችን በተሳካ ሁኔታ ለህዝቡ አሰራጭቷል፡፡
የአረበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት አርብ ሌሊት በወልቃይት ቀፍታና አድ ኸርዲ የድርጅቱ ዓላማና የትግል ጥሪ የታተመባቸውን ወረቀቶች በገፍ ለህዝቡ አድርሷል፡፡ 
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአፀ ኸርማዝና አድ ፀፀር በራሪ ፅሁፎችን ለህዝቡ የበተነው አሁን ያለፈው ቅዳሜ ሌሊት ነበር፡፡ 
በራሪ ፅሁፎቹ "እኛ አርበኞች ግንቦት 7 ነን!" የሚል ርዕስ አላቸው፤ "...እኛ ለነፃነትና ለፍትህ የቆምን፤ ለእኩልነትና ለአንድነት የተጋን፤ ለህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት እየደማንና እየሞትን የምንገኝ የህዝብ ጭቆና እና ምሬት የወለደን አርበኞች ግንቦት 7 ነን..." የሚል ሀሳብም ይገኝበታል፡፡
በአራቱ ትንንሽ ከተሞችና በሌሎች መንደሮች በበራሪ ፅሑፎች መበተን በእጅጉ የተደናገጠውና የተረበሸው የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል በአካባቢው እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
የህወሓት መከላከያ ሰራዊት የጦር አዛዦች በጥልቅ የጭንቅ ባህር ውስጥ ሰጥመው ሰራዊቱን ከበረሃ በረሃ እያንከራተቱት ነው፡፡ 
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወደ አይቀሬው ህወሓትን የመደምሰስ የመጨረሻ ፍልሚያ ሜዳ በፍጥነት እየተራመደ በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ ህወሓትም እንዲሁ ወደ ተማሰው መቃብሩ በፍጥነት እያመራ ነው፡፡

Sunday, November 29, 2015

የሕወሓት አስተዳደር አዲስ አበባን "እናሰፋለን" በሚል ሰበብ የሚሰራው ሸፍጥ ተጋለጠ (ምስጢራዊውን ደብዳቤው ይዘናል) - Zehabesha Amharic

የሕወሓት አስተዳደር አዲስ አበባን "እናሰፋለን" በሚል ሰበብ የሚሰራው ሸፍጥ ተጋለጠ (ምስጢራዊውን ደብዳቤው ይዘናል) - Zehabesha Amharic

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወልቃይት ቀፍታ፣ አድ ኸርዲ፣ አፀ ሐርማዝ፣ አድ ፀፀርና በሌሎችም ትንንሽ ከተሞች በመዘዋወር ለሁለት ተከታታይ ሌሊቶች በራሪ ፅሁፎችን በተሳካ ሁኔታ ለህዝቡ አሰራጭቷል፡፡
የአረበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት አርብ ሌሊት በወልቃይት ቀፍታና አድኸርዲ የድርጅቱ ዓላማና የትግል ጥሪ የታተመባቸውን ወረቀቶች በገፍ ለህዝቡ አድርሷል፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአፀ ኸርማዝና አድ ፀፀር በራሪ ፅሁፎችን ለህዝቡ የበተነው አሁን ያለፈው ቅዳሜ ሌሊት ነበር፡፡
በራሪ ፅሁፎቹ "እኛ አርበኞች ግንቦት 7 ነን!" የሚል ርዕስ አላቸው፤ "...እኛ ለነፃነትና ለፍትህ የቆምን፤ ለእኩልነትና ለአንድነት የተጋን፤ ለህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት እየደማንና እየሞትን የምንገኝ፤ የህዝብ ጭቆና እና ምሬት የወለደን አርበኞች ግንቦት 7 ነን..." የሚል ሀሳብም ይገኝበታል፡፡
በአራቱ ትንንሽ ከተሞችና በሌሎች መንደሮች በበራሪ ፅሑፎች መበተን በእጅጉ የተደናገጠውና የተረበሸው የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊትና የሚሊሻ ታጣቂ ኃይል በአካባቢው እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የህወሓት መከላከያ ሰራዊት የጦር አዛዦች በጥልቅ የጭንቅ ባህር ውስጥ ሰጥመው ሰራዊቱን ከበረሃ በረሃ እያንከራተቱት ነው፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወደ አይቀሬው ህወሓትን የመደምሰስ የመጨረሻ ፍልሚያ ሜዳ በፍጥነት እየተራመደ በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ ሀወሓትም እንዲሁ ወደ ተማሰው መቃበሩ በፍጥነት እያመራ ነው፡፡

Saturday, November 28, 2015

ወያኔ ሰራሽ የርስበርስ ግጭት ድግሶችን እናምክን


November 28, 2015
def-thumb
የወያኔ ስርዓት የኢትዮጵያን አስተዳደር ሲያዋቅር በህዝብ ታሪካዊ አብሮነትና ተዛምዶ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰብ ልዩነቶችን በማጉላትና ልዩነቱም የርስበርስ ጥርጣሬና ግጭት ምንጭ እንዲሆን በማድረግ ነው። ልዩነቱ የእርስ በርስ ግጭትና የረጅም ጊዜ ቁርሾ እንዲፈጥር ተደርጎ ከመዋቀሩ በተጨማሪ፣ ግጭቱ በማንኛውም ጊዜ እንዲነሳ ፖለቲካዊ ግፊት ይደረግበታል ። አንዱ ብሔረሰብ በሌላው ብሔረሰብ ክልል ውስጥ ሲሆን ባዕድነት እንዲሰማውና እንዲሰጋ፣ አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ እንዲመለከተው ለማድረግ ላለፉት 24 አመታት ሲገፋ ቆይቷል፤ እየተገፋም ነው። በዘመነ ወያኔ በየቦታው በብሔር ወይም ብሔርሰብ ስም የተነሱ ግጭቶች በሙሉ የተቀሰቀሱት በራሱ በአገዛዙ ባለስልጣኖች እንጂ በህዝቡ አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም። በተለያዩ የደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ለማባረር የተወሰዱት እርምጃዎች በሙሉ ባለስልጣኖቹ ከፊትና ከጀርባ ሆነው የቀሰቀሱዋቸው ፣ ያቀነባበሩዋቸውና የመሩዋቸው ለመሆናቸው ተጎጂዎች በግልጽ ሲናገሩ ሰምተናል።
በቅርቡ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በአስቃቂ ሁኔታ ተገድለውና ተጥለው የተገኙት የአማራ ተወላጆች የሥርዓቱን ባህሪይ ከሚያሳዩ መግለጫዎች አንዱ ነው ። እንዲህ አይነቱ አሰቃቂ ድርጊት ወያኔ ባስለጠናቸውና ባዘዛቸው ካድሬዎችና ባለስልጣኖች የተፈጸመ እንጂ በሕዝብ ተነሳሽነት የተፈጸመ አለመሆኑ ግልጽ ነው። በቅርብ የተፈጸመው ድርጊት ቀደም ሲል በመንግስት ደረጃ የተቀነባበረው አማሮችን የማፈናቀል ዘመቻ ተከታይ ስራ ነው። በወገኖቻችን ላይ በሚዘገንን መንገድ የተፈጸመው ይህ አሰቃቂ ግፍ ዘልቆ ይሰማናል። ቁጭታችንና ሀዘናችን ግን ወያኔ ወደሚፈልገው የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት መንስኤ እንዳይሆን ከፍተኛ ትዕግስትና ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
ሰሞኑን እንደገና በታሪክ ሊዘገብ ከሚችል ልዩነት ውጭ ባኗኗር፣ በባህልና ቋንቋ የማይለያዩትን የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች ቅማንትና አማራ በሚል ለማጋጨት ጥረት በማደረግ ላይ ይገኛል። ይህ ሰይጣናዊ አካሔድ በወያኔ የፖለቲካ ተንኮል እየተመራ እንዳለ የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች አሉ። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ካላንዳች መድሎና ልዩነት ሀገሪቱ ላይ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ሁሉም በየበኩላቸው የሚያደርጉትን ጥረትና ትግል ይደግፋል። በህዝባችን መካከል ያሉት ግንኙነቶች አንዱ አንዱን የሚያግዝና የሚደግፍ እንዲሆን እንጂ የእርስ በርስ የመጋጨትም ሆነ የመናቆር ምክንያት እንዳይሆን ተግቶ ይሠራል ።
ኢትዮጵያውያን ብሄርና ዘር ሳንለያይ ይህንን የወያኔ ተንኮል ችግሩ ወደባሰ ደረጃ ሳይሄድ መቋቋምና ማክሸፍ እንደሚኖርብን አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል። ይህ ታሪክዊ መተሳሰራችንንና ታላቅ ሕዝብነታችንን የማይመጥን አሳፋሪ የወያኔ ፖለቲካ እንደሀገር እንዳያጠፋን ሁላችንም በንቃትና በቁርጠኝነት መቋቋም ይኖርብናል::
አርበኞች ግንቦት ፯ ልዩነት ጌጥ እንጂ የጠብና የግጭት ምክንያት የማይሆንባት ሀገር ፥ የየብሔረሰቡ መብት ሁሉ የይስሙላ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠባት ሀገር ፥ ከነልዩነታችን በጋራ ራዕይ የምንተሳሰርባትና የምንገነባት ሀገር እንድትኖረን የሚያደርገውን ትግል ይቀጥላል። የቻልክ በአካል ተቀላቀለን። ያልቻልክ በያለህበት የወያኔ ዘራፊዎች ያሰቡትን የተንኮል ጉንጉን በመበጣጠስ ተሳተፍ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Friday, November 27, 2015

ወያኔ ሰራሽ የርስበርስ ግጭት ደግሶችን እናምክን!!! ==============================


Nov 27, 2015 Editorial

የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያ የተዋቀረችው በህዝብ ታሪካዊ አብሮነትና ተዛምዶ ላይ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰብ ልዩነቶችን በማጥበቅና ልዩነትንም የርስበርስ ጥርጣሬና ግጭት ምንጭ እንዲሆን በማለም ነው። ልዩነት የግጭትና የጠብ ምንጭ እንዲሆን ተደርጎ ነው የተዋቀረውና ብፖለቲካ ደረጃ የተገፋው። አንዱ ብሔረሰብ ሌላው ብሔረሰብ ክልል ውስጥ ሲሆን ባዕድነት እንዲሰማውና እንዲሰጋ አንዱ አንዱን በጥርጣሬ እንዲመለከተው ተደርጎ ነው ሀያ አራት አመት ሙሉ የተገፋውና እየተገፋ ያለው።
ይህም ሆኖ በዘመነ ወያኔ በየቦታው የተከሰቱ የብሔር ሌብሔርሰብ ግጭቶች በሙሉ የተቀሰቀሱት በራሱ በመንግስት ባለስልጣኖች እንጂ መቼም ህዝብ ለሕዝብ ሆኖ አያውቅም። በተለያዩ የደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች አማሮችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ለማባረር የተወሰዱት ርምጃዎች ራሳቸው ሰለባዎቹ እንደሚናገሩት ለስቃይ የዳረጋቸው ነዋሪው ሕዝብ ሳይሆን ባለስልጣናቱ መሆናቸውን በግልጽ ሲናገሩ ሰምተናል።
በቤኒሻጉልና ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሰሞኑን ይፋ መሆኑ የተነገረው በአስቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተቀብረው የተገኙ አማሮች አስከሬን መገኘቱ ታውቋል። ይህም ወያኔ ባስለጠናቸውና ባዘዛቸው ካድሬዎችና ባለስልጣኖች የተከወነ እንጂ በሕዝብ ተነሳሽነት የተፈጸመ አለመሆኑ የታወቀ ነው። ቀደም ሲል በመንግስት ደረጃ የተቀነባበረ አማሮችን የማፈናቀል ዘመቻ ተከታይ ስራ መሆኑን ለማወቅ ብዙ አዳጋች አይደለም። በወገኖቻችን ላይ በሚዘገንን መንገድ የተፈጸመው ግፍ ዘልቆ ይሰማናል:: ሊሰማንም የገባል። ቁጭታችንና ሀዘናችን ግን ወያኔ ወደሚፈልገው የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ምክንያት እንዳይሆን ከፍተኛ ትዕግስትና ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
ሰሞኑን በታሪክ ሊዘገብ ከሚችል ልዩነት ውጭ ባኗኗር በባህልና ቋንቋ የማይለያዩትን የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች ቅማንትና አማራ በሚል ለማጋጨት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ሰይጣናዊ አካሔድ በወያኔ የፖለቲካ ተንኮል እየተመራ እንዳለ የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች አሉ። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉም ካላንዳች መድሎና ልዩነት ሀገሪቱ ላይ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ሁሉም በየበኩላቸው የሚያደርጉትን ጥረትና ትግል እንደግፋለን። በህዝባችን መካከል ያሉት ግንኙነቶች ሊሆን የሚችለው እንዱ አንዱን የማገዝ እንጂ ርስበርስ የመጋጨትም ሆነ የመናቆር አይደለም።
ኢትዮጵያውያን ብሄርና ዘር ሳንለይ ይህንን የወያኔ ተንኮል ችግሩ ወደባሰ ደረጃ ሳይሄድ መቋቋምና ማክሸፍ ይጠበቅብናል። ይህ ታሪክነታችንና ታላቅ ሕዝብነታችንን የማይመጥን አሳፋሪ የወያኔ ፖለቲካ እንደሀገር እንዳያጠፋን ሁላችንም በንቃትና በቁርጠኝነት መቋቋም ይኖርብናል።
አርበኞች ግንቦት ፯ ልዩነት ጌጥ እንጂ የጠብና የግጭት ምክንያት የማይሆንባት ሀገር ፥ የየብሔረሰቡ መብት ሁሉ የይስሙላ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠባት ሀገር ፥ ከነልዩነታችን በጋራ ራዕይ የምንተሳሰርባትና የምንገነባት ሀገር እንድትኖረን የሚያደርገውን ትግል ይቀጥላል። የቻልክ በአካል ተቀላቀለን። ያልቻልክ በያለህበት የወያኔ ዘራፊዎች ያሰቡትን የተንኮል ጉንጉን በመበጣጠስ ተሳተፍ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


በጎንደር ወገራ ወረዳ የተራቡ የሰባት ቀበሌዎች ነዋሪዎችን ለመርዳት የተመደበው ገንዘብ በቆሎ ገዝተው አንዲያከፋፍሉ ለችፋንዝ ነጋዴዎች ተላልፎ በመሰጠቱ የበቆሎ ዋጋ በእጥፍ ጨምሮ ረሃቡን እንዳባባሰው የረሃቡ ሰለባ የሆኑ ዜጎች የሰቆቃ ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፡፡
የጎንደር ወገራ ወረዳ 7 ቀበሌዎች ነዋሪ የሆነ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ክፉኛ ተርቦ ወደ እልቂት እያመራ ይገኛል፡፡ የሀወሓት አገዛዝ የረሃቡን አደጋ ለመቀነስ እስካሁን የወሰደው እዚህ ግባ የሚባል እርምጃ የለም፡፡ ለህዝብ ግንኙነት ስራ ሊጠቀምበት አቅዶ ተፍ ተፍ ሲል ከሚታየው የይስሙላህ እርዳታ በስተቀር
በወገራና ዳባት ወረዳዎች የዘጠኝ ቀበሌዎችን ረሃብተኛ ህዝብ ለመርዳት በጥቅምት ወር የቀረበው 10ሺህ ኩንታል በቆሎ በአግባቡ እንዳልተከፋፈለና 10 ቤተሰብ ላለው አባውራ 10 ኪሎ ግራም ብቻ በመሰጠቱ የረሃብተኞችን ነብስ ከሞት ለመታደግ በቂ እንዳልሆነ ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
አሁን ደግሞ የረሃቡን አደጋ ከልብ ለመቀነስ ሳይሆን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ብቻ ታስቦ ለተጀመረው እርዳታ የተመደበው ጥሬ ገንዘብ ለኪንፋዝ ነጋዴዎች በመሰጠቱና ነጋዴዎቹ በቆሎ እየገዙ እንዲያከፋፍሎ በመደረጉ የአንድ ኩንታል በቆሎ ዋጋ በእጥፍ ጨምሮ ከ300 ወደ 600 መቶ ብር አሻቅቧል፡፡ እንጨትም ሆነ ከሞት የተረፉ መንቋዳ ጥጆቻቸውን ሸጠው ወይንም በምግብ እጦት በራደው ጉልበታቸው የቀን ስራ ውለው በሚያገኗት አነስተኛ ሽልንግ 1 ጣሳ በቆሎ ገዝተው ማታ ማታ ወደ ቤታቸው በመግባት ንፍሮ እየቀቀሉ ለጊዜውም ቢሆን ነብሳቸውን እንኳን እንዳያቆዩ አገዛዙ እርዳታ አደርጋለሁ ብሎ የእህል ገበያው ላይ አለመረጋጋት እየፈጠረ የረሃቡን እልቂጥ እያፋጠነው እንደሚገኝ ተጎጅዎች የሰቆቃ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማሰማት ላይ ናቸው፡፡ በነጋዴዎች እየተሸመተ በጣት ለሚቆጠሩ ረሃብተኞች መከፋፈል የጀመረው በቆሎም ከአድሏዊነት የፀዳ እንዳልሆነ ረሃብተኞች ጨምረው ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በጎንደር ወገራ ወረዳ ለሰባት ቀበሌዎች በረሃብ የተጎዱ ነዋሪዎች ዘይት በመከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን እሱም ቢሆን ከአድሏዊነትና ከሙስና የፀዳ ካለመሆኑ ባሻገር መጠኑ እጅግ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ የትኛውንም ያህል የቤተሰብ ቁጥር ይኑረው ለአንድ አባውራ አራት የቡና ስኒ ብቻ እየታደለ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በጎንደር ወገራ ወረዳ በደረሰው አስከፊ ረሃብ እና አገዛዙ ለረሃቡ እየሰጠው የሚገኘው ምላሽ አደጋውን የሚያባብስ በመሆኑ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ረሃብተኞች ቀዬዎቻቸውን እየለቀቁ እግራቸው ወደመራቸው በመሰደድ ላይ ናቸው፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ‪#‎በጎንደር‬ ከተማ ቀበሌ 17 ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች በህወሃት ልዩ ኃይል ጦር በጥይ ተደብድበው ተገደሉ፡፡ ‪#‎አንድ‬ የጠገዴ ታጣቂ ሁለት የህወሓት ፖሊሶችን ገድሎ በረሃ መውጣቱ ተዘገበ፡፡ ====================================================


በጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች በህወሃት ልዩ ኃይል ጦር በጥይ ተደብድበው ተገደሉ፡፡
ህዳር 12 2008 ዓ.ም በጣት የሚቆጠሩ የቀበሌ 17 ወጣቶች መጥምቁ ዮሃንስ አካባቢ በቀሃ ወንዝ ዳር አቅራቢያ ተሰባስበው ህዳር ሚካኤልን በጋራ በማክበር ላይ እያሉ የህወሓት ልዩ ኃይል አባላት ደርሰው ወጣቶቹን ለመበተን ድንገት በከፈቱት ተኩስ ነው ሁለቱ ወጣቶች በግፍ የተገደሉት፡፡
በጥይት ከተደበደቡት ሁለቱ ወጣቶች መካከል አንደኛው ቶሎ ነብሱ ባለመውጣቱ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለህክምና ተወስዶ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የአካባቢው ነዋሪዎች ወጥተው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል አጥር ዙሪያ በጥበቃ ላይ በነበሩት ጥቂት የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር አባላት ላይ ድብደባ በመፈፀም ቁጣቸውን የገለፁ ሲሆን የልዩ ሃይል ጦር አባላቱ ሮጠው ለጥቂት ከሞት አምልጠዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግቢና አካባቢው ሌሊቱን ከፍተኛ ግርግር ተነስቶ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንዳደረ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አንድ የጠገዴ ታጣቂ ሁለት የህወሓት ፖሊሶችን ገድሎ በረሃ መውጣቱ ተዘገበ፡፡
ህዳር 14 2008 ዓ.ም ክምሽቱ 2፡30 ላይ ሁለት ፖሊሶችን ተኩሶ በመግደል እንደታጠቀ አምልጦ ጫካ የገባው ታጣቂ ስሙ ሀጎስ ይሰኛል፡፡
በታጣቂው ሀጎስ እርምጃ የተወሰደባቸው የአገዛዙ ፖሊሶች ደግሞ ኮንስታብል አስቻልና ኮንስታብል አታለለ ይሰኛሉ፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

Thursday, November 26, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


በጎንደር ላይ አርማጭሆ በህወሓት አገዛዝ ጦር ኃይልና በገበሬዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ሰላማዊ ዜጎች በስውር በመገደል ላይ ናቸው፡፡
በጎንደር ላይ አርማጭሆ ማውራ መንደር ላይ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ቀዬዎች የተስፋፋው ወህሓትን በጦር መሳሪያ የማስወገድ እርምጃና በአካባቢው የነገሰው ከፍተኛ ውጥረት አሁንም ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የህወሓት የታጠቁ ቡድኖች ጠብመንጃ አንስተው ዱር ያልወጡ ሰዎችን ጨለማን ተገን እያደረጉ ተኩሰው በመግደል ሰላማዊ ወገኞቻችንን የጥቃታቸው ዋነኛ ኢላማ አድርገዋቸዋል፡፡
ሰሞኑን በጨለማ በጥይት ተደብድበው በግፍ ከተገደሉት በርካታ ወጣቶች መካከል የሮቢት ነዋሪ የሆነው አበበ እንየው የተባለው ይገኝበታል፡፡ ወጣቱ አበበ እንየው ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ለይ ነው የህወሓት ገዳይ ቡድን ጥይት ሰለባ ለመሆን የበቃው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በጎንደር ላይ አርማጭሆ እንዲሁም በጭልጋ ጭምር ትምህርት ቤቶችና ሁሉም የአገዛዙ መስሪያ ቤቶች ተዘግተው የስራ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል፡፡ በመሆኑም በላይ አርማጭሆና በጭልጋ ከጦር ኃይሉ በስተቀር የህወሓት አገዛዝ የፖለቲካ መዋቅር አለ ለማለት አስቸጋሪ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም በጎንደር ደምቢያ ወረዳ የሚሊሻ ጉጅሌ ኮማንደር በሆነው አራጌ የተባለ የህወሓት-ብአዴን አገልጋይ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎ አካባቢው መጠነኛ ውጊያ እንዳስተናገደ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ዜና ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ደግሞ በሰሜኑ ክፍል እንደልብ ከቦታ ቦታ መዘዋወር እጅግ በጣም ከባድ እየሆነ እንደመጣና ህዝቡ የመንቀሳቀስ ነፃነቱ ጠብመንጃ በታጠቁ የአገዛዙ ቡድኖች መገፈፉ ታወቀ፡፡


በእጅጉ እየተፋፋመ ከሚገኘው ባንዳነትን በአርበኝነት ከማስወገድ የመሳሪያ ትግል ጋር በተያያዘ ህወሓት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ባሰማራቸው ክፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሰራዊት ጦር እንዲሁም ደህንነቶቹ በየጥቂት ኪሎ ሜትሮች የርቀት ልዩነት ቁጥር ስፍር የሌላቸው የፍተሻ ኬላዎችን በማቋቋም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ሰላማዊ ዜጎችን በብርበራ ስም ክፉኛ እያዋከበ፣ እያሸማቀቀና እያሸበረ ይገኛል፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደርና ከአዲስ አበባ ወደ ወሎ በሚወስዱ ጎዳናዎች ላይ የፍተሻ ኬላዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክረው የመንገደኞችን ሰብዓዊ መብት በረገጠ መልኩ ብርበራ፣ ማዋከብና ማሸብር እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ ከአዲስ አበባ ደሴ በተዘረጋው መስመር በቅርቡ በተጀመረው ከዚህቀደም ታይቶ የማያውቅና ያልተለመደ ጥብቅ ጥበቃ፣ ቁጥጥር፣ ብርበራና በጦር መሳሪያ ማስፈራራት ጋር በተያያዘ ህዝቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በአካባቢው ገብተዋል በሚል ግምት የትግል መንፈሱ እንደተነሳሳ እና የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ውስጥ ለውስጥ እየገለፀ እንደሆነ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

ኢሳት ዜና :-

ሳሙኤል ጋዲሳ ገለታ የተባለው የደህንነት አባል ጥቅምት 03/2008 ዓ.ም ፣ በመኪና አከራይነት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን አቶ ተክሉ ቀጄላን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል እንደሆንክ ደርሸብሃለሁ በማለት አስፈራርተው 30 ሺ ብር ጽዮን ሆቴል ውስጥ ሲቀበሉ፣ ግለሰቡ አስቀድመው ለፖሊስ አመልክተው ስለነበር፣ የደህንነት አባሉ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል። ፖሊስ በገንዘቡ ላይ ማህተም በማሰራፉ የደህንነት አባሉ ድርጊቱን ሊክድ አልቻለም። የደህንነት አባሉን መያዝ ተከትሎ የኦሮምያ ክልል መስተዳደር ባለስልጣናት ድርጊቱ ገጽታችንን ያበላሻል በሚል ፣ ባለፈው ሳምንት በፖሊስ ፕሮግራም ሊቀርብ የነበረው ዝግጅት እንዳይቀርብ አስደርገዋል። የፖሊስ ምንጮች እንደሚሉት የደህንነት አባሉ በቁጥጥር ስር እንዲውል የጠቆሙ ሰዎች፣ በደህንነቶች እየተጠሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳ የደህንነት ሰራተኛው አሁንም ድረስ ማእከላዊ ታስሮ ቢገኝም፣ክስ እንዳይመሰረትበት ለማድረግ ባለስልጣናት በመሯሯጥ ላይ ናቸው።

Wednesday, November 25, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)


ሰሞኑን በወላይታ ሶዶ የተጀመረው የአርበኝነት ትግልን የሚያፋፍሙ ፅሁፎችንና ምስሎችን የያዙ ወረቀቶችን የመለጠፉ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በሙሉ በትግል ጥሪ ወረቀቶች ተጥለቅልቀዋል፡፡
"አንዳርጋቸው ፅጌ የጀመረውን ትግል እኛ እንጨርሳለን!" የሚልና ሌሎችን መፈክሮች ከምስል ጋር የያዙት ወረቀቶች በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎች ጎፋ ሳውላ፣ ቁጫ፣ ሰላም በር፣ ዳውሮና በሁሉም ቀበሌዎች በስፋት ተለጥፈዋል፡፡
በዚህ የተነሳ የአካባቢው የህወሓት ደህዴግ ሹሞች በከፍተኛ ጭንቀት በተሸበበ ስብሰባ ላይ ናቸው፡፡ በስብሰባው ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም በአርባ ምንጭና በወላይታ ሶዶ እየተቀጣጠለ የሚገኘው ህዝባዊ ትግል ከቁጥጥራቸው ወጥቶ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ አምነዋል፡፡
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ፖሊሶች በከተሞች የትግል ጥሪ ከያዙት ወረቀቶች በተጨማሪ የጦር መሳሪያም ተሰራጭቷል የሚል ስጋት አድሮባቸው ያለፈውን ሌሊት ሳይተኙ በከፍተኛ ጥበቃና ቤት ብርበራ አሳልፈውታል፡፡
በአጠቃላይ በአሁኗ ሰዓት በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳዎችና ልዩ ልዩ ቀበሌዎች ከፍተኛ ሽብር ነግሷል፡፡

TPDM POEM TESHELEM JUN 2015

Tuesday, November 24, 2015

በደቡብ ክልል በርካታ ከተሞች አርበኞች ግንቦት7 የድጋፍ ወረቀቶች ተበተኑ

ኀዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው ወጣቶች እንደገለጹት፣ በወላይታ ሶዶ ከ1 ሺ የማያንሱ በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል። ራሳቸውን ያደራጁት ወጣቶች በፖሊስ፣ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የገበያ ማእከላት የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ን ፎቶ እንዲሁም የቅስቀሳ መልእክቶችን የያዙ ወረቀቶችን በግድግዳዎች ላይ ለጥፈዋል። ፖሊሶች ወረቀቶችን በመቅደድ ተጠምደው ማርፈዳቸውን፣ በከተማው ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያ ርእስ መፍጠሩንም ወጣቶች ለኢሳት ገልጸዋል። በአርባምንጭ፣ ቁጫና ጎፋ (ሳላ) በርካታ ወረቀቶች ተበትነዋል። በእነዚህ አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተባብረው ወጣት እንደገለጸው፣ ወረቀት መበተኑ በህዝቡ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል ብለአል። ህዝቡ ወረቀቶችን በደንብ መመልከቱንና ለካ መንግስትን የሚገዳደር ሃይል እየተፈጠረ ነው የሚል አስተያየቶች እንደደረሱዋቸው አስተባበሪዎች ገልጸዋል።

በቴፒ ከተማ ውጥረት ነግሷል

ኢሳት (ህዳር 14 ፣ 2008) በደቡብ ምዕራብ ቴፒ ከተማ የተቀሰቀሰውን አስተዳደራዊ አለመግባባት ተከትሎ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው መስፈሩ ተገለጠ። በከተማዋ ላይ የተነሳው የይገባኛል አስተዳደራዊ ጥያቄ ስምምነት ባለማግኘቱ በርካታ ሰዎች በተቃውሞ ጫካ መግባታቸውንና ድርጊቱ በከተማዋ ውጥረት ማንገሱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከሚዛን ተፈሪ ወደ ቴፒ፣ ከሸሸንዳ ከተማ ወደ ቴፒ፣ ከሚሻ ከተማ ወደቴፒ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ በፌዴራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥጥር እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ታውቋል። በንግድ እንቅስቃሴዋ የምትታወቀው የቴፒ ከተማም ከወትሮ በተለየ መልኩ የስጋት ቀጠና ሆና መሰንበቷን የተከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በይፋ የተገለጸ የሰዓት እላፊ ገደብ ባይኖርም የከተማዋ ነዋሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይፈቀድላቸው ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ቴፒ ከተማ የምትገኝበት የኪ ወረዳን ለማስተዳደር በሸኮ ብሄረሰብ ተወላጆችና በሸካ ብሄረሰብ ተወላጆች መካከል ፖለቲካዊ ጥያቄ መነሳቱንና ችግሩ እልባት አለማግኘቱን የከተማዋ አስተዳደር ይገልጻል። አስተዳደራዊ ጥያቄው መግባባትን ሊፈጥር ባለመቻሉም ተቃውሞ ያስነሱ በርካታ ሰዎች ጫካ ገብተው ኣንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን፣ በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት እነዚህን ሃይሎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘመቻ ከፍቶ እንደሚገኝ ታውቋል። ይሁንና ድርጊቱ በከተማው ነዋሪ ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የተፈጠረው ችግር ፖለቲካዊ መፍትሄን እንደሚፈልግ የገለጹት ነዋሪዎች፣ የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ በተጠሩ መድረኮች አስተያየት የሰጡ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስረድተዋል። “በአደባባይ ሃሳብን መግለፅ በራስ እንደመፍረድ ይቆጠራል” ሲሉ ነዋሪዎቹ የችግሩን አሳሳቢነት ገልፀዋል። ከአመታት በፊት ጀምሮ በከተማዋ የአስተዳደራዊ ጥያቄዎች ሲነሱ መቆየታቸው ይታወሳል። ባለፈው አመት የቴፒ ወህኒ ቤትን የሰበሩ ታጣቂዎች የፖሊስ አዛዡን ጨምሮ አራት ፖሊሶች በመግደል እስረኞቹን ይዘው ወደጫካ መግባታቸው ይታወሳል። የመንግስት ሃይሎች ከእነዚህ ታጣቂዎች ጋር ለመደራደር ያደረጉት ሙከራ በድምፅ ተቀርጾ ለኢሳት መድረሱንና ይህም መዘገቡ አይዘነጋም።

ይድረስ ለሆዳችሁ ብቻ ለምታስቡ! (ህሊና ስጦታው)

በህሊና ስጦታው
ይድረስ፥
1. በጥንቃቄ ተመርጣችሁ፣ ለሆዳችሁና ለኪሳችሁ ብቻ የምታስቡ በመሆናችሁ የተለያየ ስልጣን ተሰጥቷችሁ፣ አገርንና ሕዝብን ዘርፋችሁ፣ ፎቅ እንድትሰሩና ሚሊየኔር እንድት ሆኑ ተፈቅዶላችሁ፣ እነዚህ መቶ የማይሞሉ ባለጌዎች ታዛዥ በመሆን አገርንና ወገንን የምትበድሉ የሲቪል ባለስልጣኖች፥
2. በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በሕዝብ ተመረጣችሁ ተብሎ ከየቦታው የተጠራቀማችሁ ሥራችሁም የነርሱ ብልሹ ምግባር ሕጋዊ እንዲሆን በትዕዛዝ እጃችሁን እያወጣችሁ የምታስወስኑ ብልሹ ዜጋዎች፥
3. የአገርና የወገን መመኪያ መከታ ነኝ ብለህ ቃል በመግባት መለዮ አድርገህ፣ መሣሪያ ታጥቀህ፣ በሰራዊት ውስጥ ሆነህ የምታገለግለው፣ እነዚህ የባለጌ ጥርቅምና ሌቦች በልማት ስም አገርህን ለእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ሲሻሟት፣ አንተ ኮንዶሚኒየም ስለሚሰራልህ፣ የወርቅ ማዐድኗም በአላሙዲን ስም እየተጫነ በዓለም ዙሪያ ሂሳባቸው እያስገቡ የወደፊት ቤታቸውን ሲሰሩና ፋብሪካዎች እየከፈቱ ሲነግዱ የሚቃወሙትን እየደበደብክና እየገደልክ እንደጀግና ትጎርራለህ። እናንተንም በዘር በመከፋፈል፣ ለግዳጅ ስትላኩ ወደ ተለያየ ጎሳ በመላክ ያንዳችሁን ጎሳ ሌላው በጭካኔ እንዲገለው አንዲደበድበው ያድርጋል። ግን እናንተን ምን ያህል ዝቅ አድርጎ ቢገምቷችሁ ነው ገበሬውን ለዘመናት ከሚያርስበት ቦታ በልማት ስም ተፈናቅሎ ለምን ብሎ ሲጥይቅ በናንት በጀግኖቹ ይደበደባል፣ ይገደላል። አዛዦቻችሁ በጣም የሚያሳዝኑም የሚያሳፍሩም ናቸው። ጌቶቻችሁ በዶላር ለሚያሸሹት ገንዘብ ዘብ ቆመው፣ የሰራዊቱን በጀት መበዝበዝ ስለተፈቀደላቸው እናንተን ጃስ እያሉ ወገንን ያስነክሳሉ። ለመሆኑ ታሪክ ትቶ ማለፍ ምን ያህል እንደሚያኮራና በቢሊዮን ከተዘረፈ ሐብት በላይ መሆኑ ይገባቸዋል? ለአገራቸውና ለወገናቸው በሚሠሩት መልካም ሥራ፣ ወላጆቻቸውም ልጆቻቸውም በወገን ምን ያህል ፍቅር እንደሚያድርባችውና እንደሚያኮራቸው ያውቃሉ? አይመስለኝም!
በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው በዚሁ ባልታደለ የአፊሪካ ምድር እንድነዚ እንደኛዎቹ ያለ የፖለቲካ ፓርቲ በታሪክ ተፈጥሮ አያውቅም። ነገር ግን 99% የአፍሪካ መሪዎች ሌቦችና አልጠግብ ባዮች ናቸው። ይህንንም የሚያመጣው በመጥፎ ድህነት ውስጥ ማደግ ነው። ግን የሌብነት ዕድሜን ለማራዘም ሲል የትኛውም የአፍሪካ አገር መሪ ፓርቲና ወገነንን በዘር ከፋፍሎ አያውቅም። በየትኛውም መልኩ መከፋፈል ዕድገት አምጥቶ አያውቅም። እርግጥ ሕዝብን አንድ ላይ እንዳይቆምና መብቱን እንዳይጠይቅ ያደርገዋል። የማይፈለገውም እርሱ ነው። መለዮ ለባሹ በአረቡ ዓለም እንደታየው፣ ማለት በግብጽ፣ በሊቢያ በየመን፣ መሪዎቹን በቃ፣ ለሌቦች ዘብ አንቆምም፣ የአገርና የወገን እንጂ የአረመኔዎችና የሌቦች ስብስብ፣ በዘር የሚያስቡ ሆዳሞች አገልጋዮች አይደለንም ብላችሁ የመሣሪችሁን አፈሙዝ ወደ ሌቦቹ መንደር በማዞር ስልጣኑን ለወገናችሁ አስረክቡ።

ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው


ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ ‹‹የቤተሰብ ተጠሪ ፎረም›› የሚሉ ቅፆችን በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን ለመጠርነፍ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅፁ ላይ የቤተሰብ አባላት ‹‹በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ያለ መግባባቶችን በራሳችን ለመፍታትና ብሎም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ሆነን በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የድርሻችን ለመወጣት›› በሚል ከቤተሰብ መካከል ለፖሊስ ተጠሪ እንዲወክሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህ የቤተሰቡ የፖሊስ ተወካይም ግቢው ውስጥ ተፈጠሩ የሚላቸውን ጉዳዮችና ሌሎችም መረጃዎች ለፖሊስ ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ጥርነፋው ከቤተሰብ ተነስቶ፣ ብሎክ፣ ቀጠና እና ወረዳ እያለ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ /

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የመልካም አስተዳደርና ሙስና ችግሮች ይናገራሉ | Audio - Zehabesha Amharic

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የመልካም አስተዳደርና ሙስና ችግሮች ይናገራሉ | Audio - Zehabesha Amharic

Border points between Kenya and Ethiopia closed

by Engidu Woldie Ethiopia’s top diplomat, Tedros Adhanom, gave a lengthy interview to the Voice of America’s Tizita Belachew of the Amharic service in which he once again brought shame on himself and his TPLF comrades. We will revisit here some of the ridiculous remarks he made while he was answering, or rather, evading questions by the VOA broadcaster as well as pertinent questions by listeners of the VOA, thereby unmasking who the individuals claiming to rule Ethiopia really are. [ 2189 more words. ]

Ethiopia and Kenya border closed

ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው


ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ ‹‹የቤተሰብ ተጠሪ ፎረም›› የሚሉ ቅፆችን በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን ለመጠርነፍ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅፁ ላይ የቤተሰብ አባላት ‹‹በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ያለ መግባባቶችን በራሳችን ለመፍታትና ብሎም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ሆነን በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የድርሻችን ለመወጣት›› በሚል ከቤተሰብ መካከል ለፖሊስ ተጠሪ እንዲወክሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህ የቤተሰቡ የፖሊስ ተወካይም ግቢው ውስጥ ተፈጠሩ የሚላቸውን ጉዳዮችና ሌሎችም መረጃዎች ለፖሊስ ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ጥርነፋው ከቤተሰብ ተነስቶ፣ ብሎክ፣ ቀጠና እና ወረዳ እያለ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ድምፃዊ ወርቅነህ አሰፋ "በቃ" አዲስ ዘፈን 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


በወላይታ ሶዶ በሦስቱም ክፍለ ከተሞች አርበኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን የነፃነት አርበኝነት የሚደግፉና ህዝቡን ለትግል የሚያነሳሱ መፈክሮችና ምስሎች በብዛት ተለጠፉ፡፡
ህዝቡ በአርበኞች ግንቦት 7 ሁለገብ የትግል ማዕቀፍ ውስጥ ተሰባስቦ ሁሉም በአንድት ተነስቶ ለተጀመረው ፀረ-ወያኔ፣ ፀረ-አምባገነናዊ የህወሓት አገዛዝ ፍልሚያ የየበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ የሚያስተላልፉት ፅሁፎችና ምስሎች ወላይታ ሶዶን ዳር እስከ ዳር ያጥለቀለቋት እሁድ ዕለት ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ሲሆን ትናንት ከፍተኛ ውጥረትና ግርግር በከተማዋ ሰፍኖ ውሏል፡፡
"የክልሉን አስተዳደር" ጨምሮ የአካባቢው የህወሓት-ደህዴግ ሹሞችን የተቃውሞ ፅሁፎችና ምስሎችን የያዙ ወረቀቶች በሁሉም ቦታዎች ተለጥፈው መታየት በእጅጉ አስደንግጧቸዋል፡፡ 
በአሁኑ ሰዓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ያገኙትን ወጣት ሁሉ እያፈሱ ወደ ወህኒ በማጋዝ ላይ ናቸው፡፡

በወላይታ ሶዶ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ከተለጠፉት ምስሎች የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፎቶ ይገኝበታል፡፡

Sunday, November 22, 2015

Protesters burned TPLF flag in front of the embassy gate

በገዢው የኢህአዴግ

ስርአት በሃገር መከላክያ ሰራዊት የሚገኙ ቲሞችና ጋንታዎችን በአሁኑ ሰአት የሰው የሃይል ብዛታቸው እተዳከሙ እንደሚገኙ በመከላክያ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩት መረጃ ገለፁ።
በመረጃው መሰረት በገዢው የኢህአዴግ ስርኣት በአገር መከላክያ ሰራዊት የሚገኙ ቲሞችና ገንታዎች በአሁን ሰኣት በተለያዩ ምክንያቶች የሰው ሃይል ብዛታቸው እየተዳከሙ እንደሚገኙ ከገለፁ በኃላ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በሰው ሃይላቸው የተዳከሙ ክፍሎች ለሞምላት በሚል ምክንያት ከ 4ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ውትድርና ለመግባት ማስጣወቂያ ቢያዘጋጅም ይሁን እንጂ ባሰቦው መንገድ ሊከናወን አለመቻሉ የተነሳ በተወሰኑ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶች ግን አስገድዶ ወደ ውትድርና ለማስገባት መምርያ አውርዶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በመጨረሻ የመከላከያ ሰራዊት በአሁን ግዜ በሰው ሃይል በመዳከሙ ምክንያት አዲሶች ወጣቶች መጀመርያ በምዝገባ ሂደቱ የሚነገራቸው ቃል ከነባሩ ሰራዊት ጋር ከትቀላቀሉ በኃላ የተነገራቸው ቃል ስለ ማይተግበር፤ በሰራዊት ላይ የሚፈፀም ግፍና በደል እንዲሁም በጥቅማ ጥቅም አድልዎ ስለሚበዛ ያገኘነው ፋይዳ የለም በማለት ከሰራዊቱ ሸሽተው ለመሄድ እንደሚገደዱ መረጃው አክሎ አስረድቷ።

ህወሓት ክብሩ አሰፋን ረሸነው! ====================================================


ክብሩ አሰፋ ተወልዶ ያደገው በጎንደር-ታች አርማችሆ ማሰሮ ደንብ ነው፡፡ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ዕድሜ ላይ የሚገኘው ክብሩ አሰፋ የጀግኖቹ አርበኞች አታለል አሰፋና ክፈተው አሰፋ ታናሽ ወንድም ነው፡፡

ጀግናው አርበኛ አታለል አሰፋ በ1994 ዓ.ም ወደ በረሃ ወጥቶ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተቀላቀለ ሲሆን በወልቃይትና በአርማጭሆ ለባንዳው የህወሓት ሰራዊት የእግር እሳት በመሆን መውጫና መግቢያ ነስቶታል፡፡
አርበኛ አታለል አሰፋ ከልቡ አርበኛ ነበር፤ አርበኛ አታለል አሰፋ እጅግ ጀግና ተዋጊ ነበር፤ አርበኛ አታለል አሰፋ ብልህ የጦር መሪና ጀግና አዋጊ ነበር፡፡
አርበኛ አታለል አሰፋ በደሙ ከፃፋቸው አስደማሚ የአርበኝነት ታሪኮቹ፣ አስደናቂ ጀግንነቱና አንፀባራቂ ጀብዱው መካከል 150 አርበኞችን እየመራ ተከዜን ተሻግሮ ሚያዚያ 16 1998 ዓ.ም አርማጭሆ ጎደቤ ላይ ሰፍሮ ይገኝ በነበረው የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ጠንካራ ምት በማሳረፍ የጦር ሰፈሩን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ በርካታ ቁጥር ያለው ወታደርና ዲሽቃ መማረኩ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡
ጀግናው አርበኛ አታለል አሰፋ ለአራት ተከታታይ ቀናት የህወሓትን ሰራዊት አያራወጠ በእሳት አለንጋ በመግረፍ ሲፋለም ቆይቶ ሚያዚያ 20 1998 ዓ.ም ስናር ላይ በጀግንነት ወድቆ ውድና ክቡር ህይወቱን ለአገሩ ኢትዮጵያና ከጎኑ ተሰልፈው ይዋጉ ለነበሩት ለሚመራቸው 150 ጓዶቹ ሲል ከፈለ፡፡ ስሙ ከአርማጭሆ እስከ ወልቃይት ገኖ ተሰማ፤ ጀግንነቱ በስናርና ቋራ በረሃዎች አስተጋባ፤ የአርበኝነት ድምፁ በኤርትራ ምድረ በዳዎች ሁሉ ከፍ ብሎ አስገመገመ፡፡

Saturday, November 21, 2015

" የየጁ ደብተራ…" በኤርሚያስ ለገሰ ከቅርብ አመታት ወዲህ በአከባበር እየተለወጠ የመጣውን የህውሀት እና ልጆቹን ልደት አጨንቁሮ ለተመለከተ ብዙ ነገሮችን መናገር ይችላል።

 በልሙጡ ለሚያይ ሰው የብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴግ የልደት በአላት " መወድሰ ህወሀት" እየሆኑ መሔዳቸውን በቀላሉ መታዘብ ይችላል። ህውሀቶች የየካቲት 11 እና እሱን ተከትሎ የነበሩት ሳምንታት አልበቃቸው ብሎ ህዳር 11 ( የኦህዴድ እና የሐይለማርያምን ልደት ቀን ረሳሁት) በቤቢ ሻወርነት እየተጠቀሙበት ነው። ርግጥ ነው ህውሀቶች ወገባቸውን ይዘው " እኛ በልጆቻችን ውስጥ አድረን ቡራኬያችንን ብንወስድ እናንተን ለምን አሳከካችሁ?" እንደሚሉን ይገባኛል። ባያሳክከን ጥሩ ነበር። ፈር የሳተው ቡራኬ በኢትዬጲያ ህዝብ ላይ እያሳረፈ ያለው ጫና በአይናችን ላይ እየሔደ አላሳከከንም ማለት እንደ ብአዴን አባላት ቧልት ስለሚሆንብን ነው። እናም ቢያንስ የብአዴን አባላትን የውስጥ ጩኸት እኛ ብንጮኸው ምስጋናቸው ዘግይቶም ይደርሰን ይሆናል።
1• " ከማን አንሼ!"
ብአዴን በዘንድሮው ልደቱ የማንነት ቀውስ በፈጠረው ምክንያት ያልሆነውን ሆኖ መታየት ፈልጓል። ያልሆኑትን ሆኖ የመታየት ጉጉት የመነጨው በተለያየ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የመጀመሪያው ምክንያት ባለፈው የካቲት ህውሀት የተመሰረተበት በአል ከደደቢት (መቀሌ) እስከ ሞያሌ፣ ከጐሬ እስከ ደወሌ፣ ከሞቃዲሾ እስከ ሎስ አንጀለስ በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ነበር። በልደት በአሉ በኢትዬጲያ ምድር ታይተው የማይታወቁ አንፀባራቂ ገድሎች ተደምጠዋል። የህውሀትን ታላቅነት የሚያስተጋቡ ውዳሴዎች ተሰምተዋል። ለህዝብ የሚቀርብ እዚህ ግባ የሚባል ሀሳብ ማመንጨት የተሳነው ህውሀት አልፋ እና ኦሜጋውን ያለፋት መንግስታት ሲረግምና ሲያወግዝ ተስተውሏል። የኢሳት ባልደረባ የሆነ ጋዜጠኛ ወዳጄ ሁኔታውን ለመግለጵ የተጠቀመበት ቃል በህሊና ግርግዳዬ ላይ ተለጥፋ ቀርታለች። ጋዜጠኛው " የየጁ ደብተራ ፣ ቅኔው ቢጐድልበት ቀራርቶ ሞላበት" ነበር ያለው።የህውሀት ልደትን ለመዘከር ወደ ደደቢት የተጓዘው እንግዳም ከብዙዎች ግምት በላይ ነበር። ታዳሚዎች የራሳቸውን አለም ፈጥረው በፈንጥዝያ ባሕር ውስጥ ሲዋኙ ነበር። የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን ለብቻቸው የተቆጣጠሩት ህውሀቶች " ሀገሬን አልረሳም!" በሚለው ተወዳጅ ዘፈን ሲጨፍሩ የተመለከቱ ደግሞ እስከ ዛሬም ከመገረም እንዳልወጡ አጫውተውኛል። በተለይም የጫካ ዘመኑን " እንበር ተጋዳላይ!" በሚለው ቀስቃሽ ዘፈናቸው ያሳጠሩት ዘፋኞች ተቀምጠው " ሀገሬን አልረሳም!" በሚል ኢትዬጲያዊ ዜማ መፈንጠዙ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለውን ለማወቅ አያዳግትም። እነ አቦይ ስብሀት ከዘመናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሸራተን ያገኙትን የዘፈኑ ባለቤት " ስማ አንተ! …" ( ያልጨረስኩት ቃሉን ብጠራ በጣም አስቀያሚ፣ ኢትዬጲያ ብሆን ደግሞ ሶስት ወር ስለሚያሳስር ነው) …ለማንኛውም ሽማግሌው ስብሀት " ስማ አንተ…"በማለት ያንቋሸሹትን ሰው እንዲዘፍን ሲያዙት የንቀት ደረጃቸውን የሚያሳይ ነው።

የህወሓት አሻንጉሊት የሆነው ብአዴን 35ኛ የሎሌነት ዘመኑን ለማክበር በየቦታው ድግስና ፌሽታ በማሰናዳቱ ምክንያት "አማራ ክልል" አየተባለ በሚጠራው የሚገኙ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ባለው ጦር ተወረው በአሁኑ ሰዓት ህዝብ ክፉኛ እየተዋከበና እየተሸበረ ይገኛል፡፡


ትግራይን ለማስገንጠል ነፍጥ አንስቶ የሸፈተው ህወሓት የደርግ ከህዝብ ተነጥሎ መዳከምና በወቅቱ ሌላ የታጠቀ ጠንካራ ተቀናቃኝ ኃይል አለመኖሩ የፈጠረለትን አጋጣሚ ተጠቅሞ ሀሳቡን በመቀየር መላ ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ የስልጣንና የምዝበራ አድማሱን ለማስፋት ሲያቅድ ከብሄር ፖለቲካ ጭቃ አምቦልቡሎ በአምሳሉ ከፈጠራቸው የጎሳ ድርጅቶች መካከል አንዱና ዋነኛው "ብሄረ አማራ ዴሞክሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን" እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡
ብአዴን የኢትዮጵያ አንድትን ከሚያራምደው ኢህአፓ ወጥቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ኢህዴን በህወሓት ትዕዛዝ ወደ "ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ" ተለውጦ ወደ ዘር ፖለቲካ ሸለቆ ተወርውሮ በጭንቅላቱ ተተክሎ የቆመ እና የአማራው መጨቆኛ ዋነኛ መሳሪያ ነው፡፡
ብአዴን "በአማራ ተወላጆች የሚመራ የአማራ ድርጅት" እንደሆነ አስመስሎ በአማራው ህዝብ ፊት ለመታየት ይሞክር እንጂ ዋነኛና ተቀዳሚ ዓላማው አማራውን ማዳከምና ማግለል ነው፡፡ 
ብአዴን 35ኛ ዓመት የሎሌነት ዘመኑን የደፈነው በአማራ ተወላጆች እየተመራ አይደለም፡፡ 
•ታምራት ላይኔ የጉራጌ ተወላጅ
•በረከት ስምኦን (መብራህቶም ገ/ህይት) የኤርትራ ተወላጅ
•ህላዌ ዮሴፍ የኤርትራ ተወላጅ
•ተፈራ ዋልዋ የሲዳማ ተወላጅ
•አዲሱ ለገሰ የሀረር ተወላጅ...
ሌላም ብዙ መጠቃቀስ ይቻላል አጥንት ቆጠራ የህወሓትና የአሻንጉሊት ድርጅቶቹ የእነ ብአዴን ተግባር ስለሆነ ነው አንጂ፤ ብአዴን "የአማራ ድርጅት ነኝ" እያለ ደጋግሞ ስለሚነግረን በእነሱ የዘርና የቋንቋ ፖለቲካ ስሌት ዲስኩር ፈፅሞ አለመሆኑን በትንሹም ቢሆን ለማስረዳት ተሞከረ እንጂ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዘር ሃረጉ የተመዘዘበት ግንድ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ቋንቋ ተፈጥሯዊ ስላልሆነ ፈፅሞ መለያ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያዊ ቋንቋውን አንደ ዘር መለያ ካልተጠቀመበት በስተቀር አጥንቱን ወደ ኋላ ቆጥሮ ደሙን በትክክል ሊናግ አይችልም፡፡

ነገር ግን "የአማራው ተወካይ ነኝ" የሚለን ብአዴን የአማራነትም ሆነ የኢትዮጵያዊነት ስነ-ልቦና ጨርሶ የለውም፤ የአማራም የኢትዮጵያም የለየለት ጠላት እንጂ፡፡
እነሆ ዛሬ ብአዴን በጠባቧ የህወሓት የዘር ፖለቲካ ብ

TPDM TV Special Program Nov 19 2015

Friday, November 20, 2015

ፖለቲካ በደም አይጋባም


November 20, 2015
def-thumb
ህዝባዊ ተቀባይነቱን ያጣው ወያኔ በሽፍትነት ዘመኑ ትግራይ ውስጥ ሲያደርግ እንደረነበረው ሁሉ፣ መንግስታዊ ስልጣኑን ከያዘም በሁዋላ መሰልጠን አቅቶትና እንደመንግስት ማሰብ ተስኖት፣ አገዛዜን ይቃወማሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን ዜጎች የቅርብ ቤተሰቦችና የሩቅ ዘመዶች ሳይቀር ማሰቃየት መጀመሩን ከአራቱም የአገራችን ማዕዘናት በየቀኑ የሚደርሱን ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
በቅርቡ በአርባ ምንጭ ከተማ ለአገራቸው ነጻነት በገዛ ፈቃዳቸው ተነሳስተው ታሪካዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በሞከሩ ወጣቶች ላይ የስርዓቱ ታማኝ ጥቂት የደህንነት ሃይሎች የወሰዱት እርምጃ ዘግናኝና ልብ የሚያቆስል ነው። ይህም አልበቃ ብሎ የተፈላጊ ወጣቶች መኖሪያ ቤቶች በታጠቁ የደህንነት ሃይሎች ተወረው ፍተሻ ተካሂዶባቸዋል:: እናቶች ህጻናት ልጆቻቸው ፊት “የተደበቁ ልጆቻችሁን አምጡ ” ተብለው መሳሪያ ተደቅኖባቸው፣ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል።

ESAT WWH No holds barred discussion with Ambassador Herman Cohen 19 Nove...

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) በጎንደር ወገራ ወረዳ ንዑስ ወረዳ ገደብዬ በረሃቡ ለተጎዱ ህፃናት ከለጋሾች የተሰጠው አልሚ ምግብ በአግባቡ እየተከፋፈለ እንዳልሆነ በዛሬው ዕለት ከቦታው የደረሰን መረጃ አጋልጧል፡፡ ====================================================


ከለጋሾች የተቸረው የህፃናት አልሚ ምግብ ከቦታው መድረሱን ያረጋገጡት የሰባት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጎስቋላ ገበሬ እናቶች ልጆቻቸውን አንዱን በጀርባቸው አዝለው ሌላኛውን በደረታቸው ታቅፈው በዛሬው ዕለት ከየቀዬዎቻቸው ወደ ገደብዬ ከተማ ሲጎርፉ የዋሉ ሲሆን በጣት ከሚቆጠሩት እጅግ በጣም ጥቂት እድለኞች በስተቀር ሁሉም ለማለት በሚቻል ሁኔታ አልሚ ምግቡ ሳይሰጣቸው ከረሃብና ከችጋራቸው በላይ መንገድ ብቻ ተመትተው ተመልሰዋል፡፡
አልሚ ምግቡን እንዲያከፋፍሉ የተመደቡት የህወሓት-ብአዴን ካድሬዎች በዓይኖቻቸው ብቻ በመመልከት "ህፃናቱ ስላልተራቡ አልሚ ምግቡ በፍፁም አያስፈልጋቸውም" እያሉ ወላጆችን በቁጣ ጭምር በመገሰፅ ባዶ እጃቸውን እንደመለሷቸው ታውቋል፡፡ ነገር ግን አልሚ ምግቡን ለመቀበል በመጡ እናቶች ጀርባ ላይ ተጨባብጠው ይታዩ የነበሩት ህፃናት በሙሉ በረሃብ ጠውልገው አካላቸው የከሳና ዓይኖቻቸው የጎደጎዱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከባለፀጋዎች በምፅዋት የሚገኙትን አልሚ ምግቦች በተለይም ደግሞ "ፕላምፕኔት" ሸጦ ገንዘቡን ለግል ጥቅም ማዋል በወረዳው የህወሓት-ኢህአዴግ ካድሬዎች ዘንድ የተለመደ እጅግ በጣም አሳፋሪ ተግባር እንደሆነ እና አሁንም ተከማችቶ የሚገኘው አልሚ ምግብ ለተራቡ ህፃናት የተነፈገበት ዋና ምክንያት ሸጦ የግል ኪስን ከማድለብ በማለም እንደማይዘል ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የህወሓት-ብአዴን ካድሬዎች ለተለያዩ የፖለቲካ ተልዕኮዎች ወደ ገጠር ሲላኩ ለድሆች በምፅዋት የተገኘውን "ፕላምፕኔት" ስንቅ ቋጥረው አዘውትረው ሲመገቡት መመልከታቸውን በድርቁ የተጎዱ ገበሬዎች መስክረዋል፡፡
በወገራና በዳባት ወረዳዎች 9 ቀበሌዎች ለከፋ ድርቅና ረሃብ መጋለጣቸውን በቅርቡ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

ፖለቲካ በደም አይጋባም Patriotic Ginbot 7 Editorial =========//=======


ህዝባዊ ተቀባይነቱን ያጣው ወያኔ በሽፍትነት ዘመኑ ትግራይ ውስጥ ሲያደርግ እንደረነበረው ሁሉ፣ መንግስታዊ ስልጣኑን ከያዘም በሁዋላ መሰልጠን አቅቶትና እንደመንግስት ማሰብ ተስኖት፣ አገዛዜን ይቃወማሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን ዜጎች የቅርብ ቤተሰቦችና የሩቅ ዘመዶች ሳይቀር ማሰቃየት መጀመሩን ከአራቱም የአገራችን ማዕዘናት በየቀኑ የሚደርሱን ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
በቅርቡ በአርባ ምንጭ ከተማ ለአገራቸው ነጻነት በገዛ ፈቃዳቸው ተነሳስተው ታሪካዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በሞከሩ ወጣቶች ላይ የስርዓቱ ታማኝ ጥቂት የደህንነት ሃይሎች የወሰዱት እርምጃ ዘግናኝና ልብ የሚያቆስል ነው። ይህም አልበቃ ብሎ የተፈላጊ ወጣቶች መኖሪያ ቤቶች በታጠቁ የደህንነት ሃይሎች ተወረው ፍተሻ ተካሂዶባቸዋል:: እናቶች ህጻናት ልጆቻቸው ፊት "የተደበቁ ልጆቻችሁን አምጡ " ተብለው መሳሪያ ተደቅኖባቸው፣ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል።
በአገዛዙ ዘረኛና የተጨማለቀ ፖሊሲ ተማረው ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ እርምጃ መውሰድ የጀመሩ የቴፒ ወጣቶችን ለማደን የተደረገው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ የፈደራል ፖሊስና መከላኪያ ሠራዊት በወላጆች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል። ወጣት ሴቶች እና እናቶች ርህራሄ በጎደላቸው የስርዓቱ ታማኝ ወታደሮች ተደብድበዋል፣ ተደፍረዋል፣ ታስረዋል። በሰሜን ጎንደርም እንዲሁ መብታችን ይከበር ብለው በተነሱ ወጣት ቤተሰቦች ላይ የገዢው ሃይል ታማኞች ፣ ግድያና አስገድዶ መድፈር ፈጽመዋል። እህትማማች ሴቶች መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ተገድለዋል። በወታደሮች የተደፈሩ ሴቶች ቅስማቸው ተሰብሮ ወደ አደባባይ ለመውጣት እንኳ የማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል።
በመርአዊ ከተማ መኳንንት ጸጋዬ የተባሉ በሰላማዊ ትግል ስርዓቱን የሚቃወሙ ግለሰብ፣ በልጆቻቸውና በባለቤታቸው ፊት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ የልጆችን ስነልቦና በሚነካ መልኩም ሰዋዊ ክብራቸው እንዲዋረድ ተደርጓል።

ይድረስ ለሀፍረተ ቢሱ ብአዴን እና ለ35ኛ በዓል አክባሪዎች (ግልፅ ደብዳቤ ከቂሊንጦ እስር ቤት) ፅሁፍ ዝግጅት - ዘመነ ምህረት (የቀድሞው መኢአድ ም/ፕሬዝደንት) (አቶ አሸናፊ አካሉ አበራ ሀሳብን በማንሳት አግዞኛል)


ይህንን ፅሁፍ በአማራ ስም አማራውን ለሚያቆስለውና ለህወሓት ስሪት ለሆነው ብአዴን አመራሮችና አባላት ልፅፍ ስሰናዳ ለፅሁፉ መነሻ የሆኑት ሁለት ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነሱም፡- 
1ኛ. አቶ አለምነው መኮነን (የአብአዴን የህዝብ ግንኙነት) በ01/02/08 ዓ.ም በአማራ ክልል ቴሊቪዥን ስለ 35ኛው የብአዴን በዓል አከባበር የሰጠው መግለጫ፤
2ኛ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው በደልና ጭቆና፣ በደሉን የሚሰማና አለሁ ባይ ተቆርቋ ተቋምም ሆነ መሪ አለመኖሩን ለማሳወቅ ነው፡፡
የጥንታዊና የመካከለኛውን ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ባለበት ትተን ከዘመናዊው ታሪክ ብንነሳ አብዛኛው ዘመን ገዥና የገዥ መደብ ሆኖ ኖሯል ተብሎ የሚወቀሰው የአማራ ህዝብ ነው፡፡ እገሌ የሚባለው መሪ የእገሌ ብሄር ተወላጅ እንጅ የገሌ አይደለም የሚባለው ዘር ቆጠራ ውስጥ ለመግባት አይደለም አነሳሴ፡፡ በዚህ ፅሁፍ በገዥና የገዥ መደብ ስም በአማራው ላይ በደረሰውና እየደረሰ ባለው ሰቆቃ እና አማራውን ወክዬ ስታገል 35 አመት አስቆጥሬያለሁ የሚለው ብአዴን ህዝቡን እንደማይወክል ለመሞገት ነው፡፡ የአማራ ህዝብ ትናንት ‹‹አማራ›› በተባሉ ገዥዎች፣ ዛሬ ደግሞ ‹‹አማራ ጨቆነን›› ባይ ባለጊዜዎች የመከራ ገፈት ቀማሽ ሆኗል፡፡ እየሆነም ይገኛል፡፡ አጤ ምኒልክ በኦሮሞና ደቡብ ፈፀሙት በተባለው ግፍ በአማራ ህዝብ ላይ ጣት ሲጠቆም፣ አጤ ዮሃንስ ከቦሩ ሜዳ ጉባኤ በኋላ ምላሳቸውን ስለቆረጧቸው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትግራይን በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ አይሆንም? ዛሬ እነ ጃዋር ሞሃመድ፣ መኩሪያ ቡልቻ፣ መሃመድ ሀሰን፣ የተባሉት ‹‹ምሁር›› ነን ባዮች በሚፈሰው የዘውግ ፖለቲካ ተንሳፍፈው በሚነፉት ድስኩር በስመ አማራ ስንቱ ከቤት ንብረቱ ተፈናቀለ፡፡ ተሰደደ፡፡ ተገደለ፡፡ ለሆነው ሁሉ ጥናት ተደርጎ የሚጠየቅ አካል ቢኖር የብአዴን አመራሮች ወክለንሃል በምትሉት ህዝብ ላይ ስለደረሰውና ስላደረሳችሁት ሁሉ ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች በሆናችሁ ነበር፡፡ ከእናንተ ህሊና አልባ ህይወት የእኛ በአካል መታሰር በስንት ጣዕሙ! በእርግጥ ታሪክ ፍርዱን መስጠቱ አይቀሬ ነው፡፡

ጅብ ከሄደ....
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ብሪታኒያ ከኢትዮጵያውያን ጎን እንድትቆም ጥሪ አቀረቡ
• ‹‹የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ማነስ ኢትዮጵያን ከመፍትሄ አካልነት ወደ ችግርነት እያንደረደራት ነው››
• ‹‹በቀጠናው የሚደረገው የእሳት ማጥፋት ፖለቲካ ኢትዮጵያን ወደ አለመረጋጋት እየመራ ነው›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት የብሪታኒያ አምባሳደር የሆኑትና የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው የሚመለሱት አምባሳደር ግሪጎሪ ጋር ህዳር 9/2008 ዓ.ም ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ወዳጅ የሆነችው ብሪታኒያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያውያን ጎን እንድትቆም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ከሊቀመንበሩ ጋር ለአንድ ሰዓት ያህል ውይይት ያደረጉት የብሪታኒያ አምባሳደር በወቅታዊ ሀገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት ተነጋግረዋል፡፡
ከ2007 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ያለውን የኢትዮጵያን ሁኔታ በስፋት ያስረዱት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የወጣቱ ስራ አጥነት፣ የፖለቲካው አፈና፣ ሙስና፣ የኑሮ ውድነቱና ሌሎችም ችግሮች በመቀጠላቸውንና በአሁኑ ወቅት የተከሰተው ርሃብም የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ድምር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ዜጎች ከቀያቸው ያለ አግባብ እንደሚፈናቀሉ፣ ይህንንም ሲክድ የነበረው መንግስት የተወሰኑትን መክሰሱን በጋምቤላ ክልል ዜጎችን ያፈናቀሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ላይ ራሱ መንግስት የመሰረተውን የክስ መዝገብ አስደግፈው ለአምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡

“በአማራ ብሄር ተወላጅ ወገኖቻችን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እየደረሰባቸው ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ኣጥብቄ እኮንናለው” አምዶም ገብረሥላሴ -

ዜጎቻችን በስደት ሳውዲ ዓረብያ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካ፣ ሊብያ፣ ደቡብ ሱዳንና ቤሩት የመሳሰሉ ሃገራት፤ በቀይ ባህር፣ ሜድትራንያን ባህር፣ በሲናይና ሰሃራ በረሃዎች እየደረሰባቸው ያለው መቅዘፍት ሳይበቃ በገዛ ሃገራቸው ይህን የመሰለ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ሊደርስባቸው ኣይገባም። ሃገራችን 15 ማልዮን በኣስከፊ ረሃብ በያዘበትና ሂወቱ እያጣበት ባለበት ግዜ ይህን መሰል ወንጀል መፈፀሙ የሚዘገንን ብቻ ሳይሆን የሚያሳፍር ወንጀል ነው። ብኣዴንም እወክለዋለውና ኣስተዳድረዋለው የሚለው ህዝብ ኣስከፊ ወንጀለ እየተፈፀመበት እያየ የሰው መሰውያ እንደለመደ ጣኦት ምንም ሳይል ደማቅ በዓል እያሳለፈ መሆኑ ያስገርማል። የኢህኣዴግ መንግስትም እንደዚህ ዓይነቶች ወንጀሎች የሚፈፅሙ ወንጀለኞች ይዞ ለፍርድ የማያቀርብ ከሆነ ኣስፍኘዋለው የሚለው ሰላም ከመደፍረሱ በላይ የወንጀሉ ተባባሪና ቁጥር ኣንድ ተጠያቂ ያደርገዋል። መንግስት ወንጀለኞች ባስቸኳይ ለህግ ያቅርብልን ! - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48377#sthash.zxUfwC16.dpuf

Thursday, November 19, 2015

በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ - Zehabesha Amharic

በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ - Zehabesha Amharic

Zone9 አሁንም እስረኞች ነን - ከዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ ከሚያዝያ 17 2006 ጀምሮ በፓሊስ ቁጥጥር ስርውለን የነበርነው 3 ጋዜጠኞችና እና 6 የዞን9 ጦማርያን ከአንድአመት ከሁለት ወር እና ከአንድ አመት ከ5 ወር የእስር ቆይታ በኋላ ሁላችንም ከእስር አንደተፈታን ይታወሳል፡፡ በሃምሌ ወር መጀመሪያሶስት ጋዜጠኞች እና ሁለት ጦማርያን አቃቤ ህግ ክስ አቋርጦ፣ በማስከተል አራት ጦማርያን ደግሞ ነጻ ተብለው ከእስር መለቀቃችንየሚታወስ ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስትና ላይ ሆኖ የቀረበበትን “አመጽ የማነሳሳት ክስ” እንዲከላከል መባሉም ይታወቃል፡፡


ይሁን አንጂ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ከተፈታን ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ነጻ አለመውጣታችንን የሚያሳዩ ተደጋጋሚ ተግዳሮቶች በመኖራቸውእና ሊቀየሩም ባለመቻላቸው ይህንን መግለጫ ለማውጣ ተገደናል።
1. የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ32 በሚደነግገው መሰረት “ ማንኛውም ኢትዮጲያዊ … በፈለገው ጊዜ ከአገር መውጣት ነጻነትን” በሚጻረር መልኩ “የመንቀሳቀስ መብታችን”አሁንም ተገድቧል፡፡ ለምሳሌ ጦማሪ ዘላለም ክብረት ህዳር 7/2008 በፈረንሳይ አገር በሪፓርተርስ ሳንስ ፍሮንቲየርስ (ድንበርየለሽ ጋዜጠኞች ድርጅት) ለዞን 9 ጦማር የተበረከተውን 2015 የሲቲዝንጆርናሊዝም ሽልማት የዞን9 ጦማርን ወክሎ ለመገኘት ህዳር 6/2008 ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኝም ባልታወቀ ምክንያት ከአገር መውጣት ተከልክሎ ፓስፓርቱንምተቀምቷል፡፡ በዚህም የተነሳ የሚቀጥለው ሳምንት በሚከናወነው በአለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ የሆነ የሲፒጄ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ላይ መገኘቱን እድልም በጣም አጥብቦታል ፡፡ 
2. ጦማሪ አቤል ዋበላ (የኢትዮጵያአየር መንገድ ኢንጂነር) ፣ ጦማሪ ዘላለም ክብረት (የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር) ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን( የጤና ጥበቃሚኒስትር የዳታ ኦፌሰር) እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ (በፕላን ኢንተርናሽናል የኮምኒኬሽን እና ኖውሌጅ ማኔጅመንት ሰራተኛ) ወደስራገበታችን መመለስ አልቻልንም ፡፡ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆነው መንገድ ተገደን ከአንድ አመት በላይ እስር ቤት መቆየታችን የእኛ ጥፋትአንደሆነ ተቆጥሮ ከስራ ተባረናል ፡፡ሌሎቻችንም በግል እንሰራቸው የነበሩ ስራዎችንም መቀጠል አልቻልንም ፡፡ 
3. ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከክሳችሁሙሉ ለሙሉ ነጻ ወጥታችኋል ብሎ የበየነልን ሶስት ጦማርያን ስንያዝ “ማአከላዊ” ምርመራ የተወሰደብን ፓስፓርታችን እና ሌሎች እቃዎቻችንእንዲመለሱልን ብንጠይቅም “ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባችኋል” በሚል ሰበብ እስካሁን አልተመለሱልንም

Shukri Jamal

Zone9 አሁንም እስረኞች ነን - ከዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ ከሚያዝያ 17 2006 ጀምሮ በፓሊስ ቁጥጥር ስርውለን የነበርነው 3 ጋዜጠኞችና እና 6 የዞን9 ጦማርያን ከአንድአመት ከሁለት ወር እና ከአንድ አመት ከ5 ወር የእስር ቆይታ በኋላ ሁላችንም ከእስር አንደተፈታን ይታወሳል፡፡ በሃምሌ ወር መጀመሪያሶስት ጋዜጠኞች እና ሁለት ጦማርያን አቃቤ ህግ ክስ አቋርጦ፣ በማስከተል አራት ጦማርያን ደግሞ ነጻ ተብለው ከእስር መለቀቃችንየሚታወስ ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስትና ላይ ሆኖ የቀረበበትን “አመጽ የማነሳሳት ክስ” እንዲከላከል መባሉም ይታወቃል፡፡ ይሁን አንጂ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ከተፈታን ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ነጻ አለመውጣታችንን የሚያሳዩ ተደጋጋሚ ተግዳሮቶች በመኖራቸውእና ሊቀየሩም ባለመቻላቸው ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡


Zone9
አሁንም እስረኞች ነን - ከዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ ከሚያዝያ 17 2006 ጀምሮ በፓሊስ ቁጥጥር ስርውለን የነበርነው 3 ጋዜጠኞችና እና 6 የዞን9 ጦማርያን ከአንድአመት ከሁለት ወር እና ከአንድ አመት ከ5 ወር የእስር ቆይታ በኋላ ሁላችንም ከእስር አንደተፈታን ይታወሳል፡፡ በሃምሌ ወር መጀመሪያሶስት ጋዜጠኞች እና ሁለት ጦማርያን አቃቤ ህግ ክስ አቋርጦ፣ በማስከተል አራት ጦማርያን ደግሞ ነጻ ተብለው ከእስር መለቀቃችንየሚታወስ ሲሆን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስትና ላይ ሆኖ የቀረበበትን “አመጽ የማነሳሳት ክስ” እንዲከላከል መባሉም ይታወቃል፡፡
ይሁን አንጂ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ከተፈታን ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ነጻ አለመውጣታችንን የሚያሳዩ ተደጋጋሚ ተግዳሮቶች በመኖራቸውእና ሊቀየሩም ባለመቻላቸው ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡1. የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ32 በሚደነግገው መሰረት “ ማንኛውም ኢትዮጲያዊ … በፈለገው ጊዜ ከአገር መውጣት ነጻነትን” በሚጻረር መልኩ “የመንቀሳቀስ መብታችን”አሁንም ተገድቧል፡፡ ለምሳሌ ጦማሪ ዘላለም ክብረት ህዳር 7/2008 በፈረንሳይ አገር በሪፓርተርስ ሳንስ ፍሮንቲየርስ (ድንበርየለሽ ጋዜጠኞች ድርጅት) ለዞን 9 ጦማር የተበረከተውን 2015 የሲቲዝንጆርናሊዝም ሽልማት የዞን9 ጦማርን ወክሎ ለመገኘት ህዳር 6/2008 ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኝም ባልታወቀ ምክንያት ከአገር መውጣት ተከልክሎ ፓስፓርቱንምተቀምቷል፡፡ በዚህም የተነሳ የሚቀጥለው ሳምንት በሚከናወነው በአለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ የሆነ የሲፒጄ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ላይ መገኘቱን እድልም በጣም አጥብቦታል ፡፡ 

የአዲስ አበባ ህፃናት ከቆሻሻ ላይ ምግብ አንስተው ሲመገቡ የሚያሳይ ቪዲዮ | ከተሜው ከተራበ ቆይቷል - Zehabesha Amharic

የአዲስ አበባ ህፃናት ከቆሻሻ ላይ ምግብ አንስተው ሲመገቡ የሚያሳይ ቪዲዮ | ከተሜው ከተራበ ቆይቷል - Zehabesha Amharic
እነ የሺዋስ አሰፋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መልዕክት አስተላለፉ
‹‹ርሃቡን ለዓለም ለማሳወቅ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራት አለበት››
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለህዝብ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ መልዕክቱን ያስተላለፉት በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙት የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ ሲሆኑ በተለይ ርሃቡ ለዓለም ማህበረሰብ እንዲታወቅ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበረሰቦች፣ ሚዲያውና ሌሎችም የቻሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አደራ ብለዋል፡፡
በተለይ ከመንግስት ርሃቡን የመደበቅ ባህሪ አንፃር በሌሎች ኢትዮጵያውያን በኩል ርሃቡን ለዓለም ለማሳወቅ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ ‹‹በርሃቡ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት መጥፋት አልነበረበትም›› ያሉት የፖለቲካ አመራሮቹ መንግስት ተራበ በተባለው ህዝብ ቁጥር ጨዋታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ለተራቡት መድረስ እንደነበረበትም ገልፀዋል፡፡ መንግስት የተራቡትን ቁጥርና መረጃ ስለሚደብቅም ኢትዮጵያውያን ርሃቡን ለዓለም በማሳወቅ እርዳታ እንዲገኝ ከማድረግ ባሻገር እርዳታ በማሰባሰብ ሊያግዟቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ከርሃቡ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ መልስ አለማግኘቱን፣ ህገ ወጥ የእስረኛ አያያዝ፣ የፍርድ ቤቶች ገለልተኛ አለመሆንና በአጠቃላይ የፍርድ መጓደልን በስፋት ያነሱት ሲሆን እነዚህ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው በጠነከረ መልኩ ወደ አደባባይ መውጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ችግሮችና ጭቆና ቢኖርም አጀንዳ ሆኖ መታገያ እየሆነ አይደለም ሲሉ ትዝብታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎችም መንገዶች አጀንዳዎቹ ለህዝብ መድረስ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
በላይ አርማጭሆ ሙሴ ባንብ የሚገኙ 10 የእህል ወፍጮዎች በኤሌክቲሪክ ኃይል እጥረት ሙሉ በሙሉ በመቆማቸው ባለቤቶች ለከፍተኛ ኪሳራ ህዝቡ ደግሞ ለከፋ ችግር ተጋልጧል፡፡
የወፍጮዎቹ ባለቤቶች እስከ "ክልል አስተዳደር" ድረስ የተከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ተቀርፎ ሰርተው መብላት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ደጋግመው አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ከረጅም ጊዜ መጉላላት በኋላ ለትራንስፎርመር መግዣ 1 ሚሊዮን ብር አዋጥተው እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፡፡
የወፍጮዎቹ ባለቤቶች በአሁኑ ወቅት ተስፋ ቆርተው ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ የሙሴ ባንብ ነዋሪዎች ደግሞ ለህወሓት ባላቸው የመረረ ጥላቻ ምክንያት እየተፈፀመባቸው የሚገኝ በቀል መሆኑን በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡ 
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)